“የጋራ ግብ” የመደመር አንዱ መሠረታዊ ጉዳይ ነው ስንል መደመር ልዩነትን ተሻግሮ ለጋራ ዓላማና ጥቅም መሰለፍን ስለሚመርጥ ነው።በእያንዳንዱ ልዩነት ውስጥ የጋራ ግብን መሠረት አድርጎ መተባበርና ውጤት ማምጣት ይቻላል ብሎ ታሳቢ ያደርጋል። የአድዋ ድል እውን የሆነው በውስጣችን የነበረውን ልዩነት የተሻገረ የጋራ ግብ ስለያዝን ለዚያ ስለተሰለፍን ነው።
የጋራ ግብ የጋራ ህልውናንና የጋራ ድልን ያቀዳጃል።ለጋራ ግብ መሰለፍ ጤናማ የሆነና ሚዛኑ የተጠበቀ ትብብርና ፉክክር እንዲኖርና ኃይላችን መሠብሰብ እንድንችል የሚያደርግ ነው።
መልካም ቀን ይሁንልዎ!
ኮልፌ ወረዳ 06 ብልፅግና ፓርቲ
