ወንድማማችነት እና እህትማማችነትን በማጠናቀር ጽንፈኛነትን በመታገል የኢትዮጵያን ብልፅግና እናረጋግጣለን!!
እኛ ኢትዮጵያን እንደ ድር እና ማግ የተሳሰረ እና የተሰናሰነ ማንነት ያለን ህዝቦች ነን ።ይህንም ሀገራችን የብዝሃ ማንነት፣ሃይማኖት እና ባህልን ባለቤት መሆኗ የሚታወቅ ሀቅ ነው። አባቶቻችን በአድዋ እና ካራ ማራ ላይ በዘመኑ የነበሩ ልዩነቶችን ወደ ጎን በመተው ለጋራ አላማ እና ለሀገር ነፃነት ሲሉ በጋራ መስዋዕትነት ከፍለው ሀገር ከነ ክብሩ እና ዳር ድንበሩ ጠብቀው ለዚህ ትውልድ ማስተላለፍ ችለዋል ።እኛ ኢትዮጵያውያንም የአባቶቻችንን አድዋ እና ካራ ማራ ታሪክ ዛሬ ላይ በአንድነት ፣በወንድማማችነት/እህትማማችነት እሴት፣ በህብረብሄራዊ አንድነት ፣በብዝሃ ሀይማኖት አንድ ሆነን ልዩነቶቻችንን ውበታችን አድርገን የጽንፈኝነት በጋራ መታገል ይገባል ።
የዚህ ዘመን ትውልድም የአባቶቹን ፈለግ በመከተል የኔ ብቻ ከሚል የጽንፈኝነት አስተሳሰብን ለሀገር ብልፅግና እና እድገት ፀር ሆኖ አንድ እርምጃ ወደ ፊት ሁሉት እርምጃ ወደ ኋላ ሲመልሰን የቆየ ኋላ ቀር አስተሳሰብ መሆኑን በመረዳት የዚህን ዘመን ትውልድ ትብብርን እና አብሮነትን በማጎልበት ዘመኑን የመዋጀ እና ሊመጥን የሚችል አስተሳሰብ በመገንባት ከኃላ ቀር እና ጎታች አስተሳስብ በመውጣት የጋራ እና አሰባሳቢ የሆኑ የወል ታሪኮችን በመገንባት በጋራ ለሁሉም የምትሆን ኢትዮጵያን መገንባት ለመጭው ትውልድ በሁሉም መስክ የበለፀገች እና በህብረ-ብሔራዊት መንፈስ የተገነባች ኢትዮጵያን የማውረስ አደራ የዚህ ትውልድ ኃላፊነት ሊሆን ይገባል።
መልካም ቀን ይሁንልዎ!
kolfe_prosperity_party- ብልፅግና

























