“ሙስና እና ብልሹ አሰራርን ያለምህረት በመታገል የህዝባችንን ዘላቂ ተጠቃሚነት እናረጋግጣለን !!”

ድህነትን በማስወገድ ረገድ ላባችንን ጠብ አድርገን ሰርተን ብልፅግናችን ለማረጋገጥ ተስፋ ሰጪ ጉዞ ጀምረናል፤ መዳረሻ ግባችን ሩቅ እንደማይሆን በውስብስብ ሀገራዊ፣ ቀጠናዊ እና ዓለም አቀፋዊ ሁኔታ ላይ ሆነን እያስመዘገብናቸው ያሉ ስኬቶችም ተጨባጭ ማሳያ ናቸው።

ብልፅግናን እውን ለማድረግ ቁልፉ 7/24 ሰዓት ላብን ጠብ አድርጎ መስራት ቢሆንም ይህ ብቻውን በቂ አይደለም፤ ብልፅግና የህዝባችንን ኑሮ ለማሻሻል እንጂ የጥቂት ሌቦችን ኪስ ማደለብ ባለመሆኑ ሙስናን እና ብልሹ አሰራርን ያለ ምህረት መታገላችንን አጠናክረን እንቀጥላለን።

በከተማችን አዲስ አበባ ህዝባችን በማሳተፍ የጀመረውን የፀረ ሙስና ትግል በማጠናከር፣ የአሰራር ግልፅነትን እና ተጠያቂነትን በማስፈን የህዝባችንን ዘላቂ ፍትሀዊ ተጠቃሚነት እናረጋግጣለን!

መልካም ሳምንት ይሁንልዎ ‼

Published by Admin

This site is created to strengthen the information flow between our residents and the government. Kolfe woreda 6 is located in Kolfe keranio subcity, Addis Ababa, Ethiopia.

Leave a comment

Design a site like this with WordPress.com
Get started