የብልፅግና ፓርቲ አዲስ አበባ ቅርንጫፍ ጽ/ቤት ኃላፊ አቶ ሞገስ ባልቻ በከተማችን እየተሰሩ ባሉ ስራዎች እና በወቅታዊ ጉዳዮች ዙሪያ ከክ/ከተማ እና ከወረዳ አመራሮች ጋር በቪዲዮ ኮንፈረንስ ተወያዩ

አቶ ሞገስ ባልቻ በውይይቱ ላይ እንደተናገሩት ብልፅግና ፓርቲ ከለውጡ ጀምሮ ያጋጠሙ ፈተናዎችን ወደ ድል እየቀየረ መምጣቱን አውስተው እህትማማችነትንና ወንድማማችነትን በማጠናከር የብልፅግናችን ስኬታማነት እናጎለብታለን ብለዋል።

ሁሉም ብሔር ብሔረሰቦች እኩል ተሳታፊና ተጠቃሚ የሚሆኑበት ስርዓት በመዘርጋቱ ህብረብሔራዊ አንድነትን የሚያጠናክሩ ተስፋ ሰጪ ስኬቶች መመዝገባቸውን የገለፁት ኃላፊው በአዲስ አበባ በአጭር ጊዜ ውስጥ ተጀምረው እየተጠናቀቁ ያሉ ፕሮጀክቶች ለዚሁ ማሳያ መሆናቸውን አስረድተዋል።

በብልፅግና መርህ ላይ በመቆም ፅንፈኝነትን ከህዝቡ ጋር በመታገል የከተማችን አስተማማኝ ሰላም ማስቀጠልና ልማታችንን ማፋጠን ይገባል ያሉት አቶ ሞገስ በቀጣይ ቀናት ከተለያዩ የህብረተሰብ ክፍሎች ጋር ህዝባዊ ውይይቶች እንደሚኖሩ ጠቁመዋል።

Published by Admin

This site is created to strengthen the information flow between our residents and the government. Kolfe woreda 6 is located in Kolfe keranio subcity, Addis Ababa, Ethiopia.

Leave a comment

Design a site like this with WordPress.com
Get started