ኢትዮጵያ ዛሬ ላይ ከትናንት ሲንከባለሉ የመጡና በአገር ግንባታ ሂደቱ ላይ የራሳቸውን እክል የሚፈጥሩ ጉዳዮችን በምክክርና ውይይት ለመፍታት ከፍ ያለ ሥራ ጀምራለች።

ሂደቱም የተሳለጠ እንዲሆን ከባለድርሻ አካላት ጋር ሰፋ ያሉ ውይይቶች እየተደረጉ ሲሆን፤ ዋናውን የምክክር ሂደት ለመጀመር የሚያስችሉ የቅድመ ዝግጅት ተግባራትም በመከናወን ላይ ናቸው። እነዚህን ሁነቶች እየዘገቡ ለሕዝብ ጆሮ እያደረሱ ያሉት ደግሞ የመገናኛ ብዙኃን ናቸው።

የመገናኛ ብዙኃኑ አገራዊ የምክክር ሂደቱንና ክንውኑን በተመለከተ ሁነትን ከመዘገብ የዘለለ ከፍ ያለ ሚና አላቸው። ምክንያቱም የምክክር መድረኩ ከፍ ያለ ሃሳብ የሚደመጥበት፣ ክርክር የሚደረግበት፣ የመፍትሔ ሃሳቦች የሚፈልቁበት፣ የአገር ግንባታ ሥራ አቅጣጫዎች የሚመላከቱበት፣ በጥቅሉ ትልቋን ኢትዮጵያ እውን በማድረግ ሂደት ውስጥ መላው ኢትዮጵያውያን የጋራ ጉዳይ ኖሯቸው የጋራ አገራቸውን በጋራ የሚገነቡበትን እድል ለመፍጠር የሚያስችሉ ታላላቅ እውቀቶች የሚፈልቁበት በመሆኑ ነው።

እነዚህ ታላላቅ እውቀቶች ከተለያየ አቅጣጫ፣ በተለያየ አመለካከት፣ በተለያየ አገላለጽ፣ በተለያየ ስሜት፣ በተለያየ ማንነት፣ በተለያየ የእድሜና የትምህርት ደረጃ፣ እንዲሁም በተለያየ ፍላጎትና ሁነት ውስጥ ሊነገሩና ሊቀርቡ ይችላሉ።

የእነዚህ ሁሉ ድምር ውጤት ግን ልዩነትን ማስፋት ሳይሆን ማጥበብ፤ ችግሮችን ማወሳሰብና ማግዘፍ ሳይሆን፣ ችግሮችን በእውቀትና ብልሃት ላይ ተመሥርቶ መፍታት፤ ለመወቃቀስና ለበቀል ሳይሆን፣ በትናንት ስህተቶች ላይ ተነጋግሮ በይቅርታ ለመሻገር፤ የልዩነት ምንጭ የሆኑ ጉዳዮችን ወደፊት በማምጣትና በመነጋገር ቢያንስ የጋራ የሆኑ ጉዳዮችና አጀንዳዎች በሚባሉት ላይ መግባባትን መፍጠር፤ ወዘተ. እንዲቻል ማድረግ ነው።

ራስን ትናንት ላይ ቸክሎ እንዴት ወደፊት መሻገር ይቻላል?


/በሚራክል እውነቱ/


በለውጦች መካከል ሰላማችንን ሊያደበዝዙ፣የብልጽግና ጉዟችንን ሊያደናቅፉ የሚችሉ አጋጣሚዎች በየጊዜው ሊፈጠሩ ይችላሉ፡፡ በሁሉም የአገራችን አካባቢዎች የሰላምን አየር ከመተንፈስ ይልቅ ለዘመናት በፍቅር፣ በአንድነት እና በወንድማማችነት የኖረውን ህዝብ ኢላማቸው በማድረግ፤ በህዝብ ጭንብል የራሳቸው ክብርና ዝና ለማግኘት ሲሉ ምክንያት እየፈለጉ አንዱን ብሔር በሌላኛው ላይ ለማስነሳት መሞከር፣በህዝቦች ዘንድ መጠራጠር እንዲፈጠር ማድረግ፣ ፀብ አጫሪ ንግግሮችን መናገር፣አሳሳች ፅሁፎችን መፃፍ፣ትክክለኛ ያልሆኑ ምስሎችን በማህበራዊ ሚዲያዎች መለጠፍ፣ አገር ሰላም ውላ እንዳታድር ፍላጎት የሌላቸውና የግል ጥቅማቸውን ብቻ አስበው የሚሰሩ ሀይሎች ስለመኖራቸው ጥርጥር የለውም፡፡

ሀገሪቱን ለመበታተን የሚጥሩ የእነዚህንና መሰሎቻቸውን ሀላፊነት የጎደለው እኩይ ተግባር ደባ ማጋለጥ ብሎም ከመንግስት ጎን ሆኖ ሀላፊነትን መወጣት ለነገ የማይባል የዛሬ የቤት ስራ ሊሆን ይገባዋል፡፡መልካም ስራዎችን ከማበረታታት ይልቅ ሰበቦችን እየፈለጉ ህዝብን ከህዝብ ለማጋጨት የሚፈልጉ እንቅልፍ አጥተው የሚሰሩ ሀይሎች ዛሬም በጉያችን ውስጥ አሉና፡፡

የህዝብና የሀገር ሰላም ማጣት ለማን በጀ? ችግሮች እንኳ ሲኖሩ ተቀራርበን ለችግሮቹ መፍትሔ ማምጣት ለመንግስት ወይም ለገዢው ፓርቲ ብቻ የሚተው ሳይሆን እያንዳንዳችን የመፍትሔው አንድ አካል እንደሆን ልናስብና የጋራ ምሰሶ የሆነችውን የኢትዮጵያችንን ሰላም በተልካሻ ምክንያት እንዳናጣው ልንረባረብ ይገባል፡፡

ፊትን ወደ ትናንት አዙሮ እንዴት ነው ወደ ነገ መጓዝ የሚቻለው? በእርግጥም ለጥያቄው መልስ መስጠት ያስፈልጋል፡፡በዚህ በሰለጠነ ዘመን አብሮነታችንን ማጎልበት ሲገባን የኋላውን እያነሳን ለፀብ ከተጋበዝን መደማመጥ አቅቶን አንዳችን በሌላችን ላይ ጣታችንን የምንቀስር ከሆነ በእርግጥስ የወደፊቱ እኛነታችን ዕጣ ፈንታ ምን ሊሆን ይችላል፡፡በአንድ ጉዳይ ላይ ተቸንክረን መቆም ለውጥ አያመጣም፡፡ለውጥ ማምጣት የሚቻለው በዛሬው ልፋታችንና ድካማችን ነገን አስበን ስንሰራ መሆኑን ማሰብ ተገቢ ነው፡፡

አቅጣጫችን ወደፊት ብቻ ነው፡፡ወደ ኋላ እየተመለከቱ እርስ በእርስ መነታረክ ዛሬያችንን ያባክንብናል፡፡የህዝብ ሰላምና የሀገር መረጋጋት ግድ የማይሰጣቸው አንዳንድ ጽንፍ የረገጡ ሀይሎች ወደፊት አስቦ ሀገርን ወደ ተሻለ ከፍታ ከማሻገር ይልቅ በትናንቱ አስተሳሰባቸው ተቸንክረው ይሄው ዛሬ ድረስ በዜጎች መካከል መቃቃርን በመፍጠር ላላስፈላጊ ግጭት፣ግድያና ሞት ምክንያቶች ሆነዋል፡፡

ብልጽግና ፓርቲ ራሱን በአዳዲስ አስተሳሰቦች እየለወጠ ሀገርን ከፈተና ማቅ አውጥቶ ከድህነት ወደ ብልጽግና ማማ ለማሻገር እየታተረ የሚገኝ ህዝባዊ ፓርቲ ነው፡፡ምንጊዜም የኢትዮጵያን ስኬቷን ሳይሆን ውድቀቷን፣ከፍታዋን ሳይሆን የቁልቁለት ጉዞዋን፣ጥንካሬዋን ሳይሆን ድክመቷን የሚመኙ እንቅልፍ የሌላቸው ጠላቶች ህዝቦቿን ሲሻቸው በብሔር አሊያ በሃይማኖት በመከፋፈል የማያባራ የግጭት ቅርቃር ውስጥ ለማስገባት ሲኳትኑ ዛሬም ድረስ ይስተዋላል፡፡

ዳሩ ከፍላጎት የዘለለ መቼም የማይሳካ ሕልም ብቻ ቢሆንም፡፡ይህ መሆን የሚችለው ግን በጋራ ከእኩይ ድርጊታቸው መመከትና መታገል ስንችል ብቻ ነው፡፡ሕዝባችን ለሀገራዊ አንድነት፣ ለሀገር ሰላም፣ ለልማት በጥቅሉ ለሁለንተናዊ ብልጽግና እያሳዬ ያለው ፍላጎት ከጊዚያዊ ግጭቶች ይበልጥ እንደሆነ እንጂ አንሶ አያውቅም፡፡

የኢትዮጵያዊያን የመልማት ፍላጎት ከማንኛውም ከፋፋይ አጀንዳ ይበልጣል፤ይሄ ሐቅ ነው፡፡ ይሄንን ለሺህ ዓመታት ተከባብሮና ተዋዶ የኖረን ጽኑና አስተዋይ ሕዝብ ይዘን ችግሮችን እንዳይደገሙ አድርገን እንደምንፈታቸው ብልጽግና እምነቱ ከፍ ያለ ነው።

ብልጽግና ፓርቲ ከባድ እና ህዝባዊ ሀላፊነትን የተሸከመ ፓርቲ ነው፡፡የተሸከመውን የህዝብ አደራ መወጣት የሚያስችሉ በሳልና ጊዜውን የዋጁ አመራሮችንም ስለመያዙ ጥርጥር የለውም፣ምንም እንኳ በየጊዜው ራሱን መፈተሽ ያለበት ቢሆንም፡፡

ከላይ እስከ ታች ያለው የፓርቲው አመራር ሀገራዊ እሴቶችን በተሟላ መልኩ ለማስቀጠል ትልቅ ኃላፊነት የተሸከሙ ጽኑ አመራሮች ናቸው፡፡በትንንሽ ኮሽታዎች የማይደናገጡ ይልቁንም የተጣለባቸውን ህዝባዊ አደራ ለመወጣትና መስዋዕት ለመክፈል የተዘጋጁና እየከፈሉ ያሉ የአመራሮች ስብስብ ነው-ብልጽግና፡፡

ከሚለያዩንና ለግጭት ከሚያበቁን መንስኤዎች ይልቅ አንድ የሚያደርጉን ብዙ ሺህ ምክንያቶች አሉንና አንድ ሆነን ከውስጥም ሆነ ከውጭ የኛን ትርምስ፣የሀገርን የእርስ በእርስ ግጭት ቆመው ለማየት የሚጓጉ ሀይሎች በአንድነታችን አንገታቸውን ልናስደፋቸው ይገባል፡፡

ለመላው የክርስትና እምነት ተከታዮች በሙሉ የኮልፌ ቀራንዮ ክፍለ ከተማ ወረዳ 6 ብልፅግና ፓርቲ መልካም የስቅለት በአል እንዲሆንላችሁ ይመኛል።መልካም በአል!! #GoodFriday

ስለአገር ሲባል በወንድማማችነት ስሜት ነጋችንን አብረን እናቅና!


በዜማ ያሬድ

ብዙዎቻችን ስለዛሬ ለመናገር ስናስብ ትናንት የመጣንበትን መንገድ በሚዛን ከመመልከት ይልቅ ወደየራሳችን ፍላጎት በማስጠጋት የፖለቲካ ቀመራችንን እንዳያዛባው አድርገን እንጠቀምበታለን፡፡ ትናንትን እንደየሁኔታው በመቀበል ለዛሬ መማሪያነት ያለፈ ዋጋ እንደሌለው ከማሰብ ይልቅ ዛሬያችንን እንዲያበላሽብን ነጋችንንም እንዲያጨልምብን እናደርጋለን፡፡

በአገራችን ባለፉት ዓመታት የተዘራው የሃሰት ትርክት ፍሬ አፍርቶ እርስ በእርስ መጠራጠር ውስጥ እንደከተተን፤ አንዳችን ለሌላችን እድል ከመሆን ይልቅ ስጋት እንደሆንን አድርገን እንድንቀበል የተቀበረብንን ፈንጅ ማምከን ተስኖን እርስ በእርስ የጥላቻ አዙሪት ውስጥ እንሽከረከራለን፡፡ ዛሬን ማሸነፍ ሲገባን እዛው አዘቅት ውስጥ ስንዳክር ለልጆቻችን ተስፋ ሳይሆን ስጋትን ስንጭር እንውላለን፡፡

የመጣንበት የሃሰት ትርክት አደጋው የከፋ መሆኑን ከእኛ የበለጠ ምስክር ማንም የለም፡፡ ስር የሰደደ ጥላቻ የፈጠረው ጭካኔ ዛሬ ብዙ ንጹሃንን ሰለባ እያደረገ ቀጥሏል፡፡ ይህ የሆነ ቦታ መቆም አለበት የሚል መቆርቆር ውስጥ መግባት ካልተቻለ ሁላችንም የሚጸጽተን ሌላ የባሰ ሁኔታ ውስጥ መግባታችን አይቀሬ ነው፡፡ ማንም ሰው ቀድሞ ራሱን ከተጠያቂነት ለማዳን በሚመቸው መልኩ ጣቱን ወደሌላው ለመቀሰር ከመሞከሩ በፊት እኔስ በዚህ ሁሉ ሂደት ውስጥ ቦታዬ የቱ ጋር ነበር ብሎ መጠየቅ ይገባዋል፡፡ ስህተትን በስህተት ማረም፤ ቁስልን ሌላ ቁስል በመፍጠር መሻር አይቻልም፡፡ ይልቁንስ ከድጡ ወደማጡ ወደሆነ ሁኔታ ውስጥ ከመግባት ባሻገር፡፡

ውድ አንባብያን አገራችን በውጫዊ እና በውስጣዊ ፈተናዎች ውስጥ ቅርቃር ገብታ ትገኛለች፡፡ በአንድ ጎን ከትናንት መጥፎ ታሪኩ መፋታት ያልቻለና ስህተትን ሌላ ስህተት በመስራት ማረም በሚፈልግ ትውልድ ተወጥራለች፡፡ በሌላ ጎኑ በአገሪቱ የፖለቲካ ሂደቱ ውስጥ ዘዋሪ የነበረው ሃይል ቦታውን እንዲለቅ በመደረጉ ዛሬም እኔ ከሞትኩ ሰርዶ አይብቀል አይነት አካሄድ ውስጥ በመግባት በተገኘው አጋጣሚ ሁሉ አገሪቷን ከውስጥም ከውጭም እፉኝቶች ጋር በመሆን ይገኛል፡፡ ሁሌም ቢሆን የውስጥ ሰላማችን በተናጋ ቁጥር ተጋላጭነታችንን እንደ መነሻ በመውሰድ አገር ለመድፈር ሙከራ የሚያደርጉት አገራት በአገራችን ላይ እያሳደሩ ያሉት ጫና ቀላል የሚባል አይደለም፡፡

አገሬው መገንዘብ ያለበት ይሄን ዙሪያ መለስ ፈታኝ ሁኔታ ነው፡፡ አገር ያለ ሰው ምንም ናት፡፡ አገር እኛ ነን፡፡ እኔ፣ አንተ አንቺ፡፡ እኛ ስንበረታ አገር ትበረታለች፡፡ እኛ ስንተባበር፤ በአንድነትም ስንቆም አገር ጸንታ ትቆማለች፡፡ እኛ በተዳከምን ቁጥር አገር ትዳከማለች፤ ለአደጋም ትጋለጣለች፡፡ በመሆኑም ቆም ብሎ ከራስ ፍላጎት በላይ ስለአገር….ስለ ነጋችን ማሰብ ግድ ይላል፡፡ ሰላም በሌለበት ሁሉ የመኖር ህልውና አደጋ ውስጥ ነው፡፡ ሰላም መንግስት ብቻ በሃይል የሚያስጠብቀው አይደለም፡፡ የሰላም ባለቤት ህዝብ ነው፡፡ ስለ አገር ሲባል ሁሉም ከራስ ፍላጎት እልፍ ብሎ መጨነቅ ይገባዋል፡፡

መንግስት በአገራችን ያለውን ሁኔታ ለማሻሻል ግንባር ቀደም ኃላፊነት መውሰድ እንዳለበት ከማመላከት ባሻገር በአገር ግንባታ ሂደት ውስጥ የራስ ሚናን ማየት ግድ ይላል፡፡
መንግስትን ከዚህም ከዚያም ወጥሮ አቅም ለማሳጣት የሚደረገው ጥረት ዞሮ ጉዳቱ ለራስ ነው የሚል እይታ አለኝ፡፡ አገር ብትታመስ ቀድሞ የሚጎዳው ሁሉም ነው፡፡ ዘር፣ ሃይማኖት ሰላም በሌለበት ሁሉ ማምለጫ መንገድ ሊሆኑ አይችሉም፡፡ የውጭ ሃይሎች አገራችን ውስጥ ጣልቃ ቢገቡ ምናልባትም ከሶሪያ፣ ከየመንና ሌሎች አገራት በባሰ ሁኔታ ውስጥ ነው የምንገባው፡፡ ይህ ደግሞ ሁሉንም የአገሪቱን ህዝብ አደጋ ውስጥ የሚከት እንጂ ከዚህ የሚያተርፍ ማንም የለም፡፡

ትርፍ አገኛለሁ ብሎ ከውጭ ሃይሎች ጋር በራሱ አገር ጉዳይ ያበረውም ጭምር ያኔ መግቢያ አይኖረውም፡፡ ህልውናው አደጋ ውስጥ ነው የሚሆነው፡፡ ይህን አደጋ በሁሉም አቅጣጫ ማመዛዘን ያስፈልጋል፡፡ ምን ይመጣል፤ ካልደፈረሰ አይጠራም ብሂል አይሰራም፡፡ የደፈረሰውን ማጥራት ያቃጣቸው ዛሬም አገራቸው የትርምስ ማዕከል ሆና ህዝባቸውን ወደቀደመ ሰላማቸው ለመመለስ የተቸገሩ አገራትን ማየት በቂ ነው፡፡
አንዱ በሌላው ላይ የሚቀስርበት ጊዜው አሁን አይደለም፡፡ ማንም ንጹህ የለም፡፡ ሁሉም ስህተት ሰርቷል፡፡ አሁን የሚስፈልገው እርምትና መደመር ነው፡፡ ዛሬን፣ ነገንና ወደፊትን በወንድማማችነት ስሜት ሆኖ አገር ማስቀጠል ላይ መረባረብ ያስፈልጋል፡፡ ትርክቶቻችን ዛሬያችንን እንዲያጨልሙ የነገ መዳረሻችንም እንቅፋት እንዳይሆኑ ሁሉም እንደየአቅም ጥረት ማድረግ ይጠበቅበታል፡፡

ስለአገር ሲባል በወንድማማችነት ስሜት ነጋችንን ማቃናት ያስፈልገናል፡፡ በመሆኑም ዙሪያ ገባውን ማየት ያስፈልጋል እላለሁ፡፡

አገር አገር ናት፡፡ በድካማችንም በብርታታችንም ልክ የምትመዘን ናትና አገራችንን ማቆም ላይ እንረባረብ፡፡ እናስተውል፡፡ ምናልባትም መመለስ የማንችለው ችግር ውስጥ ከመግባተችን በፊት ለአገራችን ያለንን ቀናኢነት ማሳየት ይገባል፡፡ የሃሳብ ብዝሃነት በአገር ጉዳይ ላይ በጋራ ከመቆም አያግድም ስለሆነም አገራችን እኛን የምትሻበት ወሳኝ ወቅት ላይ እንገኛለንና ልብ ልንል ይገባል እላለሁ፡፡ ስለ አገር ሲባል ችግሮቻችንን ከእኛ አቅም በላይ አግዘፍን ከማየት ተላቀን ከችግሮቻችን በላይ ያለንን እምቅ አቅም በማሰብ መፍትሄ ላይ እንረባረብ ለዚህ ደግሞ ሁላችንም ከራሳችን እንጀምር እላለሁ፡፡ ሰላም፡፡

እኔነትን አፍርሰን እኛነትን!!

#Ethiopia||


#ኢትዮጵያውያን ዕጣ ፈንታችንና ህልውነችን ያልተነጣጠለና የተሳሰረ በመሆኑ አብሮነት መተባበርና አንድነት ለየትኛውም ፈተናዎች የመውጫ ቁልፉ ነው፡፡
የጋራ ታሪካችን ጋራ ጉዟችን የሚያሳየው ስንተባበር ጠንካራና የማንደፈር ብቻ ሳይሆን ታላላቅ ገድሎችን መፈፀም የምንችል ብርቱ ህዝቦች መሆናችንን ነው፡፡

ኢትዮጵያ ማደግ መለወጥ መበልፀግ ትፈልጋለች፡፤ ይህ የህዝቦቿ የጋራ ፅኑ ፍላጎት ነው፡፡

ለማደግ ደግሞ አቅማችንን መሰብሰብ ፤አንዳችን ጋር ያለውን ተነፃፃሪ አቅም ፤ሌላችን ጋር ካለው ጋር እያቆራኘን አለም ከደረሰበት ፤ህዝባችንም ከሚገባው ከፍታ ማድረስ ይገባናል፡፡

የመለያየትና የእኔነት ዜማ በህዝቦች ስም ለሚነግዱ የፖለቲካ ነጋዴዎች ጊዝያዊ ትርፍ ካልሆነ ለህዝቡ አንዳች የሚፈይድለት ነገር የለም፡፡
በመለያየት የሚያተርፍ አንድም ህዝብ የለም!!!

በየትኛውም መንገድ በህዝቦች መሃከል አጥር ለመስራት የሚጥር ቡድንና ግለሰብ ህዝቡን ፈፅሞ አይጠቅመውም!!
የሚያዋጣን መተባበር መቀናጀት አቅማችንን መሰብሰብ ፤ያንዳችንን ጉድለት አንዳችን መሙላት ፤ተዋህደን የጋራ ህልማችንን እውን ማድረግ ነው!!
መልካም ሰኞ ይሁንልን!

በአንድ አገር ውስጥ አንድ ዓይነት አስተሳሰብ ኖሮም አያውቅም፤ሊኖርም አይችልም። ስለሆነም በሁሉም ነገር መግባባት ከቶም አይቻልም፤ምክንያቱም እያንዳንዱ ሰው የራሱ ምልከታና ግምት አለውና።

#Ethiopia ||

ሆኖም ግን ልዩነቶቻችንን ወደ ጎን በማድረግ እንደ አገር ለድርድር በማይቀርቡ ወሳኝ አገራዊ ጉዳዮች ላይ በጋራ መክረን ለአገር ቀጣይ ሰላም፣ልማትና ብልጽግና ደጀንነታችንን ልናሳይ ይገባል።

በመስቀል አደባባይ የአዲስ መንግሥት ምስረታና በዓለ ሲመት ወቅት ጠቅላይ ሚንስትር ዶ/ር ዐቢይ አሕመድ ባደረጉት ንግግር፤ በአገሪቱ የፖለቲካ ኃይሎች መካከል መግባባትን ለመፍጠር ሁሉን አካታች ውይይት ይካሄዳል ሲሉ ተደምጠዋል።

ጠቅላይ ሚንስትር ዶ/ር ዐቢይ “የፖለቲካ ሥርዓቱ የአሸናፊ ሳይሆን የመግባባት እንዲሆን አብረን እንሠራለን። በንግግር እና በምክክር ለአንገብጋቢ ችግሮች መፍትሔ እናገኛለን። አካታች ብሔራዊ የውይይት መድረክ እናካሂዳለን። ችግሮቻችንን በጠረጴዛ ዙርያ የምንፈታበት ይሆናል” ማለታቸው የሚታወስ ነው።

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ “በመጪው ዘመን ብዝኃነታችንን በጌጥነት ተቀብለን መታረቅ የሚችል ሐሳባችንን አስታርቀን መከበር የሚገባው ልዩነቶቻችችን አክብረን ህብረ ብሔራዊ አንድነታችንን አጠንክረን ወደ ከፍታ የምንተምበት ጊዜ ይሆናል። ይኸም እንዲሳካ የፖለቲካ ልዩነቶቻችንን ለማጥበብ አካታች ብሔራዊ የውይይት መድረክ እናካሂዳለን” ሲሉ ለኢትዮጵያ ህዝብ ቃል ገብተዋል።

ይህ አካታች የምክክር ሒደት ችግሮቻችንን በጠረጴዛ ዙሪያ ይፈታሉ ብለው የሚያምኑትን የሚያካትት፤ በፖለቲካ ልሒቃን መካከል ብቻ የሚደረግ ብቻ ሳይሆን የሁሉም የሕብረተሰብ ክፍሎች ተሳትፎ ያገናዘበ አጠቃላይ ሒደቱ አካታች እና አሳታፊ እንዲሁም በኢትዮጵያውያን እየተመራ ሀገር በቀል መፍትሔዎች ለማፍለቅ ታልሞ የሚከናወን ስለመሆኑ የብልጽግና ፓርቲም ሆነ መንግስት በተደጋጋሚ እየገለጸ ይገኛል።

ስለሆነም አገር ወዳድ ኢትዮጵያዊያን ለዚህ አካታች ብሔራዊ የምክክር መድረክ ስኬታማነት የየበኩላችንን አስተዋጾኦ በመወጣት የታሪክ ተካፋይ ልንሆን ይገባል።

በመደመር መንገድ/ በብልጽግናችን ጉዞ ውስጥ ለጽንፈኝነት የሚሆን ቦታ አይኖርም!

በአብዲ ኬ

ብልጽግና የሚመራበት እሳቤ ማለትም መደመር ወደ ኋላ የሚተወው አካል/ሃሳብ የለም፤ መነሻውም፡- ዛሬ ያሉንን ሐሳቦች፣ ገንዘቦች፣ ዕውቀቶች፣ የተለያዩ ኃይሎች ያላቸውን አቅም ወዘተ መሰብሰብ ነው፡፡ በዚህ እሳቤ የሚቃኘው የብልጽግና የፖለቲካ ፕሮግራም ደግሞ ከሁለቱም ጽንፎች የራቀ ሚዛን ጠብቆ የሚጓዝ የመሃል ፖለቲካ (ሴንተሪዝም)*ን ነው የሚያራምደው፡፡

የጽንፍ አካሄድ ደግሞ በፍጹም ከዚህ እሳቤ የተለየ ወይም የሚቃረን ነው፡፡ በዚህ ምክንያት ነው፤ የጊዜና የመጥራት ጉዳይ ቢሆን እንጂ በብልጽግና ቤት ጽንፍም ጽንፈኛም ቦታ አይኖረውም የምንለው፡፡

በዚህ እሳቤ የተቃኛው የብልጽግና ፓርቲ የመጀመሪያ ጉባዔም ገምግሞ አቋም ከያዘባቸውና አቅጣጫ ካስቀመጠባቸው ጉዳዮች መካከል አንዱ የሃይማኖት አክራሪነት እና የብሔር ጽንፈኝነት በማኅበረሰባችን ውስጥ የሚገኝ የቅርብ ሥጋት ነው የሚል ድምዳሜን ነው፡፡ ዜጎች በሰላም፣ በፍቅር እና በይቅርታ ተከባብረው እና ተቻችለው ሊኖሩ የሚችሉት በራሳቸው እንዲደረግ የማይፈልጉትን ነገር በማንኛውም ዜጋ ላይ እንዲደረግ ባለመፍቀድ ብቻ ነው፡፡ ማንኛውም ሰው የያዘው እምነት ትክክል ነው ብሎ እንደሚያምነው ሁለ ሌላውም ሰው እምነቴ ትክክል ነው ብሎ እንደሚያምን በመርሕ ደረጃ መቀበል አለበት፡፡ በአመለካከት ደረጃ የሌላውን ሃሳብ ማክበር ያስፈልጋል፡፡ ከእምነት አተያይ ጋር በተያያዘ በዓለም አቀፍ ደረጃ በአሥር ሺዎች የሚቆጠሩ የተለያዩ እምነቶች አሉ፡፡ ሁሉም የየራሳቸው አተያይ አላቸው፡፡ ሁሉም በራሳቸው ሚዛን ትክክለኛ መንገድ ላይ እንዲለይ ያምናለ፡፡ የእምነት ነጻነት በሀገራችን የተከበረ ነጻነት ነው፡፡ በዋልታ ረገጥ አቋም የሌላውን እምነት ማንቋሸሽ በፍጹም አይፈቀድም የሚል አቅጣጫም በግልጽ ተቀምጧል፡፡

በእምነት ሽፋን የፖለቲካ እሰጥ አገባ ውስጥ መግባትም የአክራሪነት ዝንባላ እንጂ መንፈሳዊ አቋም አይደለም የሚለው የጉባዔ ግምገማ፤ የሃይማኖት አክራሪነትን የማይታገስ ማኅበራዊ መስታጋብር ማረጋገጥ አለብን የሚል አቅጣጫም አስቀምጠዋል፡፡

ሌላውና ከሃይማኖት አክራሪነት ጎን ለጎን የሚታየው የብሔር ጽንፈኝነት ነው፡፡ ሰባ ስድስት ብሔረሰቦች በሚኖሩባት ኢትዮጵያ ለብሔረሰቦች ነጻነት እና እኩልነት ትርጉም ያለው ዋጋ አለመስጠት ነውር ነው፡፡ አንደኛው ብሔር ከሌላኛው ብሔር የሚበልጥበት ወይም የሚሻልበት አንዳችም አመክንዮ የለም፡፡ ሰዎች ከሰዎች እንደማይበልጡ ሁለ አንደ ብሔር ከሌላው ብሔርም አይበልጥም፡፡ ሁለም ሰው ባለው ነገር የራሱ ከፍታ አለው፡፡ ይኸ ደግሞ ከሌላው እንዲያንስ ያደርገዋል፡፡ የእኔ ብሔር ብቻ የሚለው አስተሳሰብ ጽንፈኝነት ነው፡፡ ጽንፈኛ ብሔርተኝነት ለኅብረ ብሔራዊ ወንድማማችነት እና እኅትማማችነት ሁነኛ ዕንቅፋት ነው፡፡ በብሔር ጽንፍ የተመረዙ ሰዎች የራሳቸውን ነገር ብቻ ትክክል ነው ብለው ስለሚያምኑ በሌላው ብሔር ላይ ለሚፈጸም ማንኛውም ቀውስ ኃላፊነት አይወስደም፡፡ ስለሆነም የሃይማኖት አክራሪነትም ሆነ የብሔር ጽንፈኝነት ለሰው ልጆች ሰላምና ደኅንነት፣ ለሀገራችን ዕድገትና ብልጽግና ፀር መሆናቸውን አውቀን፣ ሕዝባችንን ማንቃት አክራነትንና ጽንፈኝነትን የማይታገስ ማኅበረሰብ መፍጠር ይኖርብናል፡፡

ከሰሞኑም በተለያዩ ቦታዎች ብቅ ብቅ የሚሉ ምልክቶች ለማንም ብሄርና ሃይማኖት ሳይሰጡ፤ በዚሁ አቅጣጫ መሰረት ሁሉም ግልጽ አቋም ይዞ እንዲታገላቸው ማድረግ ያስፈልጋል ባይ ነኝ፡፡
ቸር እንሰንብት!!

ህዝብ ያነሳቸው ቅሬታዎች በፓርቲው ጠንካራ ክትትል መፍትሔ ያገኛሉ፤


/በሚራክል እውነቱ/


የብልግጽና ፓርቲ በአገር አቀፍ ደረጃ ከህብረተሰቡ ጋር ባደረገው የውይይት መድረኮች በርካታ ችግሮች ተነስተዋል።ህብረተሰቡ በዕለት ተዕለት እንቅስቃሴው ለስራ እንቅፋት ሆነዋል ብሎ ያመነባቸውን ጉዳዮች በሙሉ ለነገ ሳያሳድር በውይይት መድረኩ አንስቷል።

በፓርቲውና በመንግሥት ትኩረት ይሻሉ፣ ፈጣን ምላሽ ሊሰጣቸው ይገባል ያላቸውን ጉዳዮች ሁሉ አንድም ሳያስቀር በነፃነት ማንሳት ብቻ ሳይሆን ፈጣን ምላሽ ከመንግስት ማግኘት እንደሚፈልግም ህዝቡ አጽንኦት ሰጥቶ አሳስቧል።

በእርግጥ ከህብረተሰቡ የሚነሱ አስተያየቶችና ቅሬታዎች እንደየአካባቢው ነባራዊ ሁኔታ የተለያዩና ሰፊ ቢሆንም አብዛኞቹ ግን ተመሳሳይነት ያላቸው ናቸው። በተለይም ከኑሮ ውድነት፣ከሰላምና ጸጥታ፣ ከአገልግሎት አሰጣጥ፣ ከፍትሃዊ ተጠቃሚነት ወዘተ ከመሳሰሉት ጋር ተያይዞ የተነሱት ናቸው።

ብልጽግና ፓርቲ የተነሱትን ችግሮች በየፈርጃው በመለየት የማያዳግም መፍትሄ ለመስጠት ጠንካራ አቅጣጫ በማስቀመጥ ለተግባራዊነቱ ክትትል እያደረገ ይገኛል። በእርግጥ ህዝቡ በየመድረኮቹ ችግሮች ናቸው ያላቸውን እንደ ፓርቲም አስቀድሞ ለይቶ አቅርቧቸው ነበር።

በፓርቲው የተለዩትንም ሆነ ህዝቡ በየመድረኮቹ ያነሳቸውን ፈተናዎች ለመሻገር በጠንካራ የፓርቲ ዲሲፕሊን እንደሚሠራና ሕዝብም በዚሁ ጉዞ ተሳታፊና ተባባሪ እንዲሆን ጭምር ጥሪ ማድረጉ የሚታወስ ነው።

ብልጽግና ፓርቲ እንደ ችግር የተነሱትን ጉዳዮች መሠረታዊ መንስኤያቸውን በመለየት ችግሮችን ከስር መሠረታቸው ለመፍታት የሚያስችል አቅጣጫ የሚከተል መሆኑን አስምሮበታል።

በእርግጥም ህዝቡ በምሬት ሲያነሳቸው የነበሩ አንዳንድ መሠረታዊ የሆኑ ጉዳዮች ጊዜ የሚሰጣቸው እና በይደር የሚቆዩ እንዳልሆኑ የሚታወቅ ነው፤ለምሳሌ ያህል ከኑሮ ውድነት ጋር የተያያዙት ጊዜ የሚሰጣቸው አይደሉም።

ስለሆነም ሕዝቡን ከገጠመው አስከፊ የኑሮ ጫና ለማላቀቅ፣ የአገልግሎት አሰጣጥ ችግርና የመሳሰሉትን በጣም ፈጣንና ግልጽ የሆነ አሠራር ዘርግቶ ወደ መፍትሄ እርምጃ መግባት ያስፈልጋል።በእያንዳንዱ ጉዳይ አስቀድሞ መረጃዎችን በመልቀቅ ህግን ተከትለው በማይሰሩ አካላት ላይ ደግሞ ተገቢውን የእርምት እርምጃ መውሰድ ይገባል።

ሌላው በየመድረኮቹ በህዝቡ ዘንድ በከፍተኛ ምሬት የተነሳው ጉዳይ እና በፓርቲው ጊዜ ሳይሰጠው ሊሠራ የታሰበው የመልካም አስተዳደር ጉዳይ ነው። ብልጽግና ፓርቲ ይሄንና ሌሎችንም ችግሮች ለመፍታት በእቅድ አካቶ የሚሠራ መሆኑ መሆኑን ለህዝቡ አሳውቋል።

ኢትዮጵያውያንን ለማንበርከክ የተቀረጸው የአሜሪካ ረቂቅ ሕግ


#cancelHR6600

ኢትዮጵያ በለውጥ ሐዲድ ውስጥ የምትገኝ አገር ነች፡፡ ዜጎቿ ነገን አስበው ዛሬ ላይ እየተጉ ይገኛሉ፡፡ በኢትዮጵያ ሁለንተናዊ ለውጥ ንዴት ውስጥ የገቡ አካላት ደግሞ ለውጡን ለማደናቀፍ አያሌ ማስፈራሪያዎችንና ዛቻዎችን እንዲሁም ማዕቀቦችን እንጥላለን ሲሉ ይደመጣሉ፡፡

ኢትዮጵያ ትናንትን አልፋ ዛሬ ላይ የደረሰችው በምዕራባዊያን ቀቢጸ ተስፋ ሳይሆን አገር ወዳድ ኢትዮጵያን በከፈሉት መስዋዕትነት መሆኑ ሊረሳ አይገባውም፡፡ ዛሬን ተሻግረን ነገ ላይ የምንደርሰውም በዜጎች ሁለንተናዊ የመለወጥ ወኔና ቁርጠኝነት ነው፡፡

በኢትዮጵያ ላይ ማዕቀብ በመጣል ተፅዕኖ ለማድረግ በአሜሪካን ኮንግረንስ አባላት እየተቀነቀነ የሚገኘውን ኤች.አር 6600 እና ኤስ 1399 ረቂቅ ሕግ እንዳይጸድቅ ኢትዮጵያውያን፣ ትውልደ ኢትዮጵያውያን እና የኢትዮጵያ ወዳጆች በያሉበት ድምጻቸውን ማሰማት ይኖርባቸዋል፡፡

በኢትዮጵያ ላይ የሚጣል ማንኛውም ማዕቀብ በፈለግነው ልክ እንዳንሮጥ እንቅፋት የሚሆነን፣ ኢትዮጵያውያንን ለማንበርከክና የበለጠ የኢኮኖሚ ጫና ውስጥ ለመክተት ያለመ በመሆኑ ይህ ሴራ እንዲከሽፍ እንደከዚህ ቀደሙ ሁሉ ኢትዮጵያውያን በአንድ ሊቆሙ ይገባል፡፡

ኤች.አር 6600 እና ኤስ 1399 ረቂቅ ሕግ ይዘት ኢትዮጵያን ሁለንተናዊ በሆነ መልኩ የሚጎዳ ከመሆኑ ባሻገር የህወሃት የሽብር ቡድን አገራችን ላይ ያደረሰውን ኪሳራ እና የሰብዓዊ መብት ጥሰት እውቅና የማይሰጥና ፍጹም አድሎዓዊ ስለመሆኑ አስረጂ አይሻም፡፡ ስለሆነም ሕጉ ለህወሃት ጥፋት እውቅና እንደመስጠትና በኢትዮጵያውያን ላይ የደረሰውን ሁለንተናዊ በደል ወደጎን እንደመተው የሚቆጠር ነው፡፡

በተለያዩ አካባቢዎች የሚኖሩ ኢትዮጵያዊያን የሚያደረጉት እንቅስቃሴዎች እንዳሉ ሆነው ይህን ረቂቅ ለማስቆም ኢትዮጵያውያን፣ ትውልደ ኢትዮጵያውያን እና የኢትዮጵያ ወዳጆች ከዚህ ቀደም እንደሚያደርጉት ሁሉ ፊርማዎችን በማሰባሰብ፣ ሰላማዊ ሰልፍ በማድረግ የተቃውሞ ድምጻቸውን በማሰማት እንዲሁም በልዩ ልዩ መንገዶች ይህ ሕግ እንዳይጸድቅ ማድረግ ያስፈልጋል።

ህጉ እንዳይጸድቅ አጋዥ ሊሆኑ የሚችሉ አሜሪካዊያን የሴኔት አባላትን እና የወዳጅ ሀገራት መንግሥታትን ባለን የዲፕሎማሲያዊ ግንኙነት መሰረት በማነጋገር በአሜሪካ መንግሥትና በኮንግረንሱ ላይ ተጽዕኖ ማድረግ የሚያስፈልግበት ጊዜ ላይ በመድረሳችን በትኩረት ልንወጣው የሚገባ አጀንዳችን መሆኑን ለአፍታም ቢሆን መዘንጋት የለብንም፡፡

አሜሪካ በኢትዮጵያ ላይ እንዲህ አይነቱን ረቂቅ ህግ ማዘጋጀት የፈለገችበት ምክንያት ግልጽ ነው፡፡ መንግስት በአሸባሪው የህወኃት ቡድን ላይ የወሰደውን አገርን ከብተና የማዳን እርምጃ ለአሜሪካዊያን አልዋጥላቸው ማለቱን የአሜሪካ ባለስልጣናት በተለያየ መንገድ እየጠቀሱ መሆኑ ግልጽ ነው፡፡

የኢትዮጵያን እውነታ መረዳት የማይፈልጉት የአሜሪካ አንዳንድ ባለስልጣናት ዛሬም ኢትዮጵያውያንን ያንበረክካል ብለው ያሰቡትን እርምጃ ሁሉ ለመውሰድ እየተረባረቡ ይገኛሉ፡፡ ኤች.አር 6600 እና ኤስ 1399 ረቂቅ ሕግም የዚህ ፍላጎታቸው አንድ ማሳያ ነው፡፡ ከዚህ ባሻገር ግን ይህ ሕግ የኢትዮ-አሜሪካን ለዘመናት የቆየ ወዳጅነት ላይ ጥያቄ የሚያስነሳ ይሆናል።

ኤች.አር 6600 እና ኤስ 1399 ረቂቅ ሕግ ኢትዮጵያ ላይ የሚደረግ ኢኮኖሚያዊ፣ ፖለቲካዊ እና ወታደራዊ ማዕቀብ በመሆኑ ዓላማው ምን እንደሆነ ለመገንዘብ አያዳግትም፡፡ በመሆኑም የኢትዮጵያ መንግስት የጀመረውን የሰላም፣ የልማት እና የዴሞክራሲ ለውጥ ሂደት እንቅፋት የሚሆነውን ረቂቅ ህግ ኢትዮጵያውያን፣ ትውልደ ኢትዮጵያውያንና መላው አፍሪካዊያን በተለመደው የአንድነት መንፈስ የተቃውሞ ድምጻቸውን በማሰማት መቀልበስ ይገባቸዋል፡፡

/በሚራክል እውነቱ/

ዛሬ ህዝብ የምናወያየው ለጠቅላላ እውቀት ወይንም ተወያይተዋል ለመባል አይደለም፤በተጨባጭ የእቅድ ግብዓት ለማድረግ ነው

የብልጽግና ፓርቲ ምክትል ፕሬዚዳንት ክቡር አቶ አደም ፋራህ በአዲስ አበባ ደረጃ እየተካሄደ ባለው የህዝብ ውይይት መክፈቻ ወቅት ከተናገሩት የተወሰደ፡-

 ዛሬ ህዝብ የምናወያየው ለጠቅላላ እውቀት ወይንም ተወያይተዋል ለመባል አይደለም፤በተጨባጭ የእቅድ ግብዓት ለማድረግ ነው፤

 የአዲስ አበባ ሕዝብ ከ1997አንስቶ በሀገራችን ዴሞክራሲ እንዲዳብር ሁሉን አቀፍ ትግል በማድረግ እንዲሁም በሁለት ሺ አስራ ሶስት ዓ.ም በነቂስ ወጥቶ በመመረጥ የበኩሉን ጉልህ አስተዋጽኦ አበርክቷል።

 የአዲስ አበባ ሕዝብ በድርቅና በጦርነት ለተጎዱ አካባቢዎች ድጋፍ በማድረግ ፣የሀገር መከላከያ ሠራዊት የኋላ ደጀን መሆኑን በተግባር ለማረጋገጥ በተመሣሣይ በዘላቂነት በዘላቂነት ሁለንተናዊ ድጋፍ እያደረገ የሚገኝ ሲሆን በተጨማሪም ለልዩ ልዩ ዓለም አቀፋዊ ስብሰባዎች እንግዶች ሲመጡ አስፈላጊውን ሁሉ ድጋፍ በማድረግ የሀገራችንን ገጽታ በበጎ ጎኑ እየገነባ ያለ ሕዝብ ነው።

 አዲስ አበባን የቱሪዝምና የኢንቨስትመንት መዳረሻ ከተማ ለማድረግ ብልጽግና ፓርቲ የላቀ ትኩረት ሰቶ እየሰራ የሚገኝ ሲሆን ለዚህም ተፈጻሚነት መላው የከተማው ነዋሪ ድጋፍ ማድረግ የሚኖርበት ፖለቲከኞች እና የማሕበረሰብ አንቂዎች ከከፋፋይ ሃሳቦች እራሳቸውን አርቀው ለከተማዋ ሁለንተናዊ ዕድገት በአንድነት መቆም ይገባቸዋል፡፡

 ከለውጡ ወዲህ ብልጽግና ፓርቲ አዲስ አበባ ከተማችን የብልፅግና ተምሳሌት የሀገራችንን የፖለቲካ ፣የኢኮኖሚ እንዳሁም የዲፕሎማሲ ማዕከል እንድትሆን እየተሰራ ነው ፤ ለዚህም በርካታ ተጨባጭ ስራዎችን አከናውኗል አሁንም ነዋሪው ከፓርቲውና ከመንግስት ጎን ተቀራርቦ መስራ ይኖርበታል፤

Design a site like this with WordPress.com
Get started