ዜማ ያሬድ
አንድ ሰው ከውልደቱ እስከ እድገቱ ባለው ጊዜ የራሱ፣ የቤተሰቡ፣ የአካባቢው፣ ብሎም በትምህርት ቤት ህይወቱና በቅርበት የሚመለከተው ባህሪ ውህድ ውጤት ነው፡፡ ከዚህ አኳያ አንድ ሰው በህይወት ዘመኑ ከቤተሰቡ ከወረሰው ባህሪ ብቻ ሳይሆን በዙሪያው የሚያድግበት አከባቢም ተጽዕኖ ያሳድርበታል፡፡ የሰው ልጅ በአካል፣ በስነምግባርና በእውቀት መልማት የሚችለው ከልጅነት ጀምሮ በሚያልፋቸው መንገዶች መሆኑ የሚያጠያይቅ ጉዳይ አይሆንም፡፡ ሰውን መርዳትና ለሰው መኖርም አብሮ ከሚወለድ ሰውኛ ባህሪ ባሻገር ከቤተሰብ፣ ከጓደኛ፣ ከሚያድጉበት ማህበረሰብ፤ ከሚከተሉት እምነትና ከሚያራምዱት የህይወት ፍልስፍና የሚቀዳና የሚለመድ መልካም ምግባር ነው፡፡ የበጎ ፈቃድ አገልግሎትም ከራስ ውስን ሃብት ቆርሶ ለሌላ የሚሰጥ ጊዜ፣ ጉልበትና እውቀት በመሆኑ በዚህ መልካም ምግባር ውስጥ ለመሳተፍ የበጎ ፈቃደኛው ማንነትና እምነት ወሳኝ ነው፡፡
በአገራችን የበጎ ፈቃድ አገልግሎት ፅንሰ ሃሳብና ጠቀሜታን በክረምት በሚደረግ መርሃ ግብር ብቻ ተወስኖ የቆየ ቢሆንም አሁን አሁን በወጣቱ ዘንድ በተለይ ባህል ወደመሆን እየተሸጋገረ መጥቷል፡፡ በአገራችን የበጎ ፈቃድ አገልግሎት ያለበት ሁኔታ በተለያየ ፈርጁ የሚጠቀስ ነው፡፡ በግልና በቡድን ሆነው አልያም የበጎ አድራጎት ተቋማት ጋር በመሆን በተለይ የሰው ድጋፍ የሚፈልጉና አቅመ ደካማ የሆኑ ሰዎችን በሆስፒታሎች የሚገኙ ህሙማን የሚንከባከቡ በጎ ፈቃደኞች እንዳሉ ይታወቃል፡፡ ጎዳና የወደቁ ወገኖቻችን የሚያነሱ፤ የተራዙትን የሚያለብሱ፣ የተራቡትን የሚያበሉ በርካታ ወጣቶች እየተፈጠሩ ነው፡፡
በጎ ፈቃድ አገልግሎት ከክረምት መርሃ ግብር ወጥቶ ሰፋ ባለ ሁኔታ አመቱን ሙሉ በመተግበር ለአገር ገፅታና ለህብረሰተባዊ ለውጥ በዘላቂነት መጠቀም ያስፈልጋል፡፡ በአገራችን የበጎፈቃድ አገልግሎት እንደዜግነት ግዴታ ተወስዶ ሁሉም እንዲሳተፍ የሚያበረታታ አሰራር ቢፈጠር የተሻለ ለውጥ ማምጣት ይቻላል የሚል እምነት አለኝ፡፡
ወጣቶቹ በበጎ ፈቃድ አገልግሎት መሰማራታቸው የሚኖረውን ህብረተሰባዊ ፋይዳ በሚገባ በማስረዳትና በማደራጀት የአገር አቅም እንዲሆኑ ማድረግ ይጠበቃል፡፡ አገራችን የበርካታ ወጣቶች አገር ሆና ሳለ ወጣቶችን በአግባቡ መጠቀም አለመቻል ትልቅ አገራዊ አቅምን እንደማባከን መሆኑን በመረዳት ለነገ ሳይባል በስር ነቀል የአስተሳሰብ ለውጥ በመታገዝ ወደ ተሻለ ሁኔታ መሻገር መቻል አለበት፡፡
የበጎ ፈቃድ አገልግሎት የአንድ ወቅት የለብ ለብ ስራ ብቻ ሳይሆን መሆን ያለበት ዓመቱን ሙሉ ወጣቱ እያሰበበት የሚቆይና የዜግነት ግዴታውና ማህበራዊ ሀላፊነቱ አድርጎ የሚወስደው መሆን አለበት፡፡ ከክረምት ጊዜው ባለፈ በዓመቱ ያለውን የእረፍት ጊዜ ማህበረሰቡን ማገልገል ላይ ሊያውለው ይገባል፡፡ ይህ ጉዳይ አገራዊ በሆነ እቅድና መነቃቃት መመራት ጭምር ይገባዋል፡፡ የበጎ ፈቃድ አገልግሎት አገር መገንባት ላይ ሊያተኩር ይገባል፡፡ ስለ ኢትዮጵያዊ አንድነትና ወንድማማችነት ማስተማር፣ ኢትዮጵያዊነትን መገንባት ላይ ያተኮሩ ህብረተሰባዊ ማነቃቃቶች ላይ በመስራት ለአገር ግንባታ የሚጠቅም መሰረት መጣል ያስፈልጋል፡፡ ለዚህ ደግሞ የበጎ ፈቃደኝነት ስራ ትልቅ መድረክ ነዉ፡፡ የበጎ ፈቃድ አገልግሎት ከችግኝ ተከላ እና ከክረምት ትምህርት ማስተማር መሻገር መቻል አለበት፡፡ ወጣቱን ስለአንድነት ማስተማር አለበት፡፡ የክረምት በጎ ፈቃድ አገልግሎት ሲታሰብ ችግኝ መትከል ብቻ አይደለም ወደ ሰው አዕምሮ ግንባታ ጭምር መምጣት አለበት፡፡ የበጎ ፍቃድ አገልግሎት ሰፋ ብሎ መታሰብ አለበት፡፡
የበጎ ፍቃድ አገልግሎትን ለብልጽግና ጉዞ መሳካትና ለህብረተሰባዊ ለውጥ ወሳኝ በመሆኑ ለዛ መጠቀም ይገባል፡፡
መንግስት የበጎ ፈቃድ አገልግሎትን የሚያበረታቱ አመቺ ሁኔታዎችን በመፍጠር አሰራሮችን በመዘርጋትና የበጎ ፈቃደኞችን በማበረታታት የበጎ ፈቃድ አገልግሎትን ፋይዳ በማብራራት ለህበረተሰባዊ ለውጥ ለመጠቀም መትጋት ይገባዋል፡፡ አገራችን እንደሌላ አገራት ዜጎች በበጎ ፈቃድ አገልገሎት መስክ የሚሰማሩ ወጣቶችን በማስፋትና ከአገር አቀፍ ወደ አህጉር አቀፍ ብሎም ዓለም አቀፍ ደረጃ በማሳደግ ሌሎች አገሮችን ጭምር ሄዶ ማገልገል የሚችል ሰብዓዊነትን የተላበሰና የፓን አፍሪካኒዝም ጽንሰ ሀሳብን የሚያቀነቅን ዜጋ እንዲፈጠር መስራት ያስፈልጋል፡፡
የግልና የመንግስት ተቋማት በበጎ ፈቃድ አገልግሎት ላይ ተሰማርተው ህብረተሰባቸውን ሲያገለግሉ ለነበሩ ወጣቶች በስራ ገበታም ሆነ ተያያዥ ጉዳዮች ቅድሚያ በመስጠትና ከሁሉ በላይ ተግባራቸዉን በማበረታታት የበጎ ፈቃድ አገልግሎት እያለሙ የሚለሙበት ዋጋ ያለው የህይወት ዘመን ሰናይ መስክ መሆኑን በተጨባጭ መደገፍ ይገባል፡፡
እያለሙ የሚለሙበት ትውልድ ተሻጋሪ አገልግሎት