“8 ሰአት ሰርተን እንለወጣለን ወይ?”ከአዲስ አበባ ምክር ቤት አባላት ለተነሳው ጥያቄ ከንቲባ ወ/ሮ አዳነች አቤቤ የሰጡትን ምላሽ ያደምጡ ዘንድ ጋብዘኖታል

ሰላም፡- ባለ ውድ ዋጋ ሀገራዊ አጀንዳ


የሰላም መስፈን ከግለሰብ አንስቶ ለማንኛውም ማህበረሰብና ሀገር ፋይዳው እጅግ ከፍ ያለ መሆኑንና የሰላም ዋጋው እንዲሁ ውድ ለመሆኑ በርካቶችን ያግባባል፡፡ ይህን የሰላም እውነታ ብዙዎች ደጋግመው በተለያየ መንገድ ከተራ ግለሰቦች አንስቶ እስከ ሃይማኖት መሪዎችና በሰላም ዙሪያ ጥልቅ ጥናትና ምርምር ያደረጉ የታላላቅ የምርምርና ጥናት ማዕከላትና ትምህርት ተቋማት ምሁራን በንግግራቸው አብዝተው ከመናገር ባለፈ የየዕለት ስብከት ያደረጉትና ብዛት ባላቸው የፅሑፍ ስራዎቻቸው ከትበው ከማስቀመጥ እስከ ድምፅና ምስል መረጃዎችና ማስረጃዎች የተካተቱበት ዶክመንተሪዎች የተሰሩበትና እየተሰሩም ያሉበት የአለማችን በግልፅ የሚታይ እውነታ ነው፡፡

ይህንኑ የሰላም ነባራዊ ሀቅ በንግግር ሰምቶ ለመቀበልም ይሁን በሰላም ዙሪያ የተደረጉ ጥናትና ምርምርን መሰረት አድርገው የተፃፉ ስራዎችን ለማንበብ ፍላጎት በማጣትም ይሁን አንብቦም እውነታውን ለመቀበል የተቸገረ አካለ ካለ እንኳ ታሪክን ወደኋላ ሄዶ መፈተሸ ሳያስፈልገው የምንገኝበትን አሁናዊውን ሀገራዊና አለማቀፍ ነባራዊ ሁኔታ በጥቂቱ በማየትና በማጤን ብቻ ስለሰላም አስፈላጊነትና የሰላም ዋጋን ውድነት በሚገባ መረዳትና መተንተን ያስችለዋል፡፡ በተለይ እንደሀገር ሀገራዊ ሰላምን በሚገባ ጠብቆ ማዝለቅ ካለመቻል ጋር ተያይዞ የሚፈጠር ሀገራዊ ቀውስና የሰላም እጦት የአንድን ሀገር ዜጎች በተናጠልም ይሁን በአጠቃላይ የሚያስከፍለውን ከፍተኛ ሰብዓዊና ቁሳዊ መሰዋዕትነትና ውድ ዋጋ በጥልቀት መረዳትና ሊኖሩ የሚችሉ ሁሉንም አይነት የሰላማዊ መንገድ አማራጮች ለመጠቀም ቅድሚያ መስጠት ይኖርብናል፡፡ በዚህም ለሰላም የሚከፈልን ዋጋ ከፍተኛነትና እጅግ ውድ መሆን ለመረዳትና በምትኩ የተሻለ አማራጭ የሆነውን እና ከባድ ዋጋ መክፈል ሳይጠበቅብን ዝቅ ባለ ዋጋ ሀገራዊ ሰላማችንን በመጠበቅ ሀገሪቱንና ዞጎቿን ካላስፈላጊ ኪሳራ የመጠበቅ አማራጭን መረዳት ይቻላል፡፡

ለአብነት እንደሀገር የዜጎችን የረጅም ጊዜ ማህበራዊ፣ ኢኮኖሚያዊና ፖለቲካዊ ጥያቄዎችን ተገቢውን ምላሽ እንዲያገኙ ለማስቻልና ሀገሪቱንና ዜጎቿን ከተደቀነባቸው የህልውና አደጋ ለማላቀቅ የተጀመረውን ሀገራዊ የለውጥ ጉዞ ከጅምሩ አንስቶ ለማደናቀፍ ሞክሮ ያልተሳካለት አሸባሪው የህወሓት ቡድን በስልጣን ዘመኑ ያላጠናቀቃቸውን ሀገር የማፍረስ ውጥኖቹን በተለየ መንገድ በሚከተለው ፅንፈኛ የሴራ ፖለቲካ ለማስቀጠል በከፈተው ጦርነት ከፍተኛ ውድመት እያስከተለ ይገኛል፡፡ በሀገሪቱና በዜጎቿ ላይ ያደረሳቸው በደሎቹ በይቅርታ ታልፈው የሀገራዊ ለውጡ አካል እንዲሆን በሆደሰፊነት በተደጋጋሚ የቀረበለትን ሀገራዊ ጥያቄ ንቆና ረግጦ በመውጣት ሀገራዊ ለውጡን ለመቀልበስና ያጣውን ማዕከላዊ ስልጣኑን ለማስመለስ በሰሜኑ የሀገሪቱ ክፍል በከፈተው አውዳሚ ጦርነት እየተከፈለ ያለውን ከባድ መሰዋዕትነት በማየት ስለሰላም ፋይዳ
መገንዘብ ይቻላል፡፡

ከሀገራችን ወጣ ብለን በመካከለኛው ምስራቅ ሀገራት የተቀጣጠለውን የፀደይ አቢዮት ተከትሎ በቀጠናው ሀገራት በተካኬዱ አውዳሚ ጦርነቶች በተከሰተ ከፍተኛ የሰላም እጦት ዜጎቻቸውን ውድ የሆነውን የህይወት መሰዋዕትነት ከማስከፈል ጀምሮ ሀብት ንብረታቸውን በማውደም ሳይገደብ ሀገራቱን ጭምር በማፈራረስና እድለኛ ሆነው በህይወት የተረፉትን ሀገር አልባ አድርጎ ለአስከፊ ስደትና መከራ የዳረገበትን ገሃድ የወጣ እውነታ ማየት ይገባል፡፡ በዚህም ሰላምን አብዝተን ስንናገረውና ስንሰብከውም ይሁን ስለሰላም አስፈላጊነት በተለያዩ መንገዶች የሚተላለፉ መልዕክቶችን ስንታደም ለንግግር ፍጆታ ከመጠቀምና የይስሙላ ከማድመጥ ባሻገር ለግለስብም ይሁን ለሀገር ህልውና እውን መሆን ሰላም የሚኖረውን ከፍተኛ ፋይዳና የሰላምን ውድ ዋጋ ባገናዘበ አግባብ መሆን ይኖርበታል፡፡

በመሆኑም ስለሰላም በተረዳነው ልክ ሰላማችንን ለማስጠበቅ ሁላችንም የበኩላችንን ድርሻ ልናበረክት ይገባል፡፡ በተለይ የሰላም ጉዳይ የሁላችንም ጉዳይ አድርገን ሰላምን ለማስፈንና ለማስቀጠል አዎንታዊ ንግግር ከማድረግ በትንሹ ከሚጠበቅብን ግዴታ አንስቶ በአጠቃላይ ለሀገራችን ሰላምና ህልውና ጊዜና ሃብትን ጨምሮ እስከ ህይሀት መሰዋዕትነት በሚከፈል ውድ ዋጋ ለሰላም በሚደረግ ተግባራዊ አስተዋፅኦ እንደሀገር ወዳድ ዜጋ የነቃ ተሳትፎ በማድረግ ኃላፊነታችንን መወጣት ይኖርብናል፡፡

እንደሀገር ወዳድ ዜጋ ዘላቂ ሰላም የሰፈነባትን ሀገር ለመፍጠር ስለሰላም ያለንን አረዳድ ግንዛቤ ከማጎልበትና አድማሱን ከማስፋት በተጨማሪ ሁላችንም የሚጠበቅብንን ሰፊ ተሳትፎ በማድረግ ተግባራዊ አስተዋፅኦ ማበርከት ይጠበቅብናል፡፡ ስለዚህ ከመኖሪያና ከስራ ስፍራችን አንስቶ የየአካቢያችን ሰላም እውን እንዲሆን ሁላችንም የሚጠበቅብንን ሀገራዊ ግዴታና ኃላፊነት በመወጣት በሰላም ዙሪያ ጠንካራ ሀገራዊ አንድነት መፍጠር ይኖርብናል፡፡ በተመሳሳይ ሁላችንም እንደግለሰብ ለሰላም ከምናበረክተው የየበኩላችን አስተዋፅኦ ጎን ለጎን ሌሎች እንዲሁ የሰላምን ዋጋ ተረድተው ከሀገራዊ ሰላማችን ጎን እንዲሰለፉና እንደዜጋ ሀገራዊ ግዴታን በኃላፊነት እንዲወጡ ማድረግ ይገባናል፡፡ በፈድሉ ጀማል

prosperity

በብልጽግና እሳቤዎች የማይፈቱ ችግሮች የሉም፤


መላው የአገራችን ህዝቦች የውስጥና የውጭ ጠላቶቻችንን በብቃት በመመከት አገራችን የጀመረችውን የለውጥና የከፍታ ጉዞ በጽናት በማስቀጠል ብሎም የተሳሳቱ ትርክቶችን ለማረም፣ ዘላቂ ሰላምን ለመገንባትና ብሄራዊ መግባባትን እውን ለማድረግ ፓርቲው ባለፉት አራት የለውጥ አመታት በየደረጃው ከፍተኛ ጥረት ሲያደርግ ቆይቷል::

ፓርቲያችን ፍትሀዊ ተጠቃሚነትን፣ አብሮነትን፣ የአንዱ ስኬት የሌላው ስኬት፣ የአንዱ ህመም የሌላው ህመም እንደሆነና እድልና እጣፈንታችንም አንድ ላይ መሆኑን የሚያሳዩ የፖሊሲ ሀሳቦችን በማቅረብ እንደ አገር ቀላል የማይባሉ ለውጦችን ማምጣት ተችሏል፡፡

እንደ ሀገር ያደሩ ችግሮችን ለመፍታት በቁርጠኝነት እየተሰራ መሆኑ ባያጠያይቅም ከሚፈለገው ደረጃ ደርሶ ለማዬት ግን የሁላችንም ርብርብና ገደብ የለሽ ተሳትፎ ያስፈልጋል፡፡

በእርግጥ ችግሮቹ በአንድ ጀንበር የማይፈቱ ግን ደግሞ መጪው ግዜ ብሩህ ተስፋ የሚታይበት እንደሆነ ጥርጥር የለውም፡፡ ከእውነት ጋር መጋፈጥ መርሆው አድርጎ እየተንቀሳቀሰ የሚገኘው ብልጽግና ችግርን በመሸሽ ሳይሆን ችግርን አውቆ በማከም ላይ ተመስርቶ እየሰራ ይገኛል ፡፡

የብልጽግና እሳቤዎች ጥልቅ፣ ከትውልድ ወደ ትውልድ የሚሸጋገሩ፣ እውነትንና እውቀትን መሰረት ያደረጉ፣ የችግሩን መሰረት በጥልቀት የሚፈትሹና ለኢትዮጵያ የከፍታ ጉዞ ሁነኛ መፍትሄዎች በመሆናቸው ህዝቡ እነዚህን ሀቆች አውቆ ከፓርቲው ጎን መሰለፍ ይኖርበታል፡፡

Prosperity

ኢሬቻ የኦሮሞ ህዝብ ባህልና ወግ መገለጫ


ኢሬቻ በእርጥብ ሣር ይወከላል፡፡ኢሬቻ የኦሮሞ ህዝብ ባህልና ወግ መገለጫ ነው። ከፖለቲካዊ ጉዳዮች ጋር የሚያያይዘው አንዳችም ነገር የለም። እናም በዕለቱ ይህን በዓል ለማክበር የሚወጣው የኦሮሞ ህዝብ እንዲሁም በበዓሉ ላይ የሚገኝ ታዳሚ ስለ ሰላም፣ መቻቻልና አንድነት ለፈጣሪው ምስጋና በማቅረብ ለሰላማዊ አከባበሩ መትጋት ይኖርበታል።

በየአመቱ መስከረም ወር ላይ የሚከበረው የኢሬቻ በአል በዘንድሮው ዓመትም/2015 ዓ/ም በአዲስ አበባና በቢሾፍቱ ሆራ አርሰዲ በደማቅ ስነ-ስርአት ይከበራል፡፡ ይህ ክብረ በአል በኦሮሚያ ብሔራዊ ክልላዊ መንግስትም ትኩረት ከተሰጣቸው ህዝባዊ በአላት አንዱ ነው፡፡የክልሉ መገለጫ ባህላዊ ስርአት እንደሆነም በስፋት ይገለፃል፡፡

ኢሬቻ ማለት ማምለክ እና ማመስገን ማለት ነው፡፡ ይሄን ስላደረክልኝ፤ክረምቱ ተጠናቆ ለበጋው ወራት በሰላም ስላሸጋገረን አመሠግናለሁ እየተባለ ፈጣሪ የሚመሰገንበት ነው፡፡ በእሬቻ ላይ ደግሞ የበለጠ የሚንፀባረቀው ባህላዊነቱ ነው፤ የኦሮሞ ትልቁ ፀሎት የሚባለው ምረቃ ነው። ምረቃውን ደግሞ ክርስቲያኑም፣ ሙስሊሙም፣ፕሮቴስታንቱም ሆነ የሌላ ዕምነት ተከታይ አባቶች ለህዝቡ ያደርሳሉ፡፡ ከዚህ ለመረዳት የሚቻለው በበዓሉ የሁሉም እምነት ተከታዮች የሚገኙና እሬቻ ሁሉንም ሃይማኖት የሚያሳትፍ ባህል እንደሆነ ነው፡፡

የእሬቻ በዓል የሚውልበት ቀን በበዓሉ አቆጣጠር መሰረት ከመስቀል ደመራ ጋር ይገናኛል ማለት ይቻላል፡፡ ምክንያቱም ይህ ህዝባዊ በዓል ከመስቀል ደመራ ማግስት ባለው እሁድ ቀን ነው የሚሆነው፡፡

ወቅቱ የአበባና የልምላሜ ወቅት ትልቅ ተስፋ የሚታይበት ስለሆነ ለዚህ በቅተናል ተብሎ ነው የሚታሰበው፡፡
ኢትዮጵያ በምትባለው ሰፊና ትልቅ ማዕቀፍ ውስጥ የሚኖር እያንዳንዱ ዜጋ የእኔ ነው የሚለው ሀገሩን ወይንም ምድሩን ብቻ ሳይሆን ህዝቡንም ጭምር ነው፤ ህዝቡ ለሚከተለው ማህበራዊ እሴቶቻችንና ባህልም ባለቤት ነው።

እንዲህ ዓይነት አስተሳሰብ በመያዝ የጋራ እሴቶቻችንን በጋራ ማክበርና እውቅና መስጠት ሀገራዊ አንድነትን ለመገንባት እና በሰዎች መካከል ፍቅርና መተሳሰብን ለመዝራት ይረዳል ባይ ነኝ።

በየዓመቱ መስከረም ወር ላይ የሚከበረው የእሬቻ በዓል በመጪው ቅዳሜ በአዲስ አበባ “ሆራ ፊንፊኔ”፤ ከነገ በዕለተ እሁድ ደግሞ በቢሾፍቱ “ሆራ አርሰዲ” በርካታ ኢትዮጵያዊያን በተገኙበት በደማቅ ሁኔታ ይከበራል፡፡

በአንድነትና በፍቅር የእሬቻን በዓል ለማክበር በርካቶች ከትውልድ ቀያቸው ወደ አዲስ አበባ እየተመሙ ይገኛሉ፡፡አዲስ አበባም ይህንኑ በዓል ለማክበር ከተለያዩ ቦታዎች የሚመጡ እንግዶችን ለመቀበል ሽር ጉዷን ተያይዘዋለች፡፡

ህዝቡ ለቀኑ ያደረሳቸውን አምላካቸውን የሚያመሰግኑበት፣ለህዝባቸውና ለሀገራቸው ፀሎት የሚያደርጉበት፣እርስ በእርስ የሚደጋገፉበትና የሚተሳሰቡበት፣ወንድማማችነታቸውን የበለጠ በተግባር የሚያሳዩበት በዓል ነው-እሬቻ፡፡

የእሬቻ በዓል በሰላም እንዲከበርና የማንም ፖለቲካ ሀይል አጀንዳ ማስፈጸሚያ እንዳንሆን ህዝቡ በተለይ ደግሞ ወጣቶች ከጸጥታ ሀይሉ ጎን በመሆን ለሰላም ያላቸውን አጋርነት ሊያሳዩ ይገባል እላለሁ፡፡ /በሚራክል እውነቱ/

መልካም የእሬቻ በዓል !

prosperity

ጽናት እና አንድነት የድላችን መሰረቶች ናቸው!


በሚራክል እውነቱ


ወቅቱ ከጠላት ጋር ፊት ለፊት የገጠምንበት ነው፡፡ ኢትዮጵያዊያን በአንድነት የሚነሱበትና ጠላትን እስከ መጨረሻው ተፋልመው ነጻነታቸውን የሚያውጁበት ጊዜ ላይ ይገኛሉ። ሽብርተኛው የትህነግ ኃይል በአማራና በአፋር ክልሎች ዘልቆ በመግባት ያለማቋረጥ የበርካታ ንጹሃንን ህይወት መቅጠፉም አይዘነጋም፡፡ ህወኃት በርካቶችን ለአካል ጉዳት ከመዳረጉም በላይ የአርሶ አደሩን ሀብትና ንብረት የዘረፈ ዓይን ያወጣ ወንበዴ ቡድን ነው፡፡ ቁጥሩ ቀላል የማይባል ህዝብ ከቀዬው እንዲፈናቀል ምክንያት ሆኗል፡፡
ከኢትዮጵያዊያን በተሰበሰበ ግብር የተሰሩ መሠረተ ልማቶች በሽብር ቡድኑ አማካኝነት ከጥቅም ውጭ ሆነዋል፡፡ የትህነግ የሽብር ቡድን በኢትዮጵያና ህዝቦቿ ላይ የፈጸመው ግፍ በእኩይነቱ ሁሌም በታሪክ የሚታወስ ይሆናል፡፡

የትህነግ የመጨረሻ ግቡ ኢትዮጵያ እንደነ ይጎዝላቪያና ሶሪያ ፈራርሳ ማየት እንደሆነ በአፈቀላጤው በኩል ማወጁ ይታወቃል፡፡ ለዚህም ይረዳው ዘንድ ከውስጥ ባንዳዎችና ከውጭ ተላላኪ ሃይሎች ጋር በመሆን አገር ለማጥፋት ሲሰራ ቆይቷል፤ ዳሩ ባይሳካለትም፡፡ በእርግጥ አገር ወዳዱ የአገራችን ህዝብ እስካለ ድረስ ኢትዮጵያ ልትፈርስ አትችልም፡፡ ታሪክም የሚያረጋግጥልን ይሄንኑ ነው፡፡ አፍራሾች ይፈርሳሉ እንጂ ኢትዮጵያ ፈርሳ አታውቅም፡፡

በአሸባሪው ህወኃት በኩል ሲሰነዘሩ የቆትን ጥቃቶችን መመከት የተቻለው ኢትዮጵያዊያን ከዳር ዳር በመነሳትና ከመከላከያ ሰራዊታችን ጎን በመሰለፍ፣ያልቻለ ገንዘቡንና ስንቅ በማዘጋጀት በአንድነት በመነሳት ነው። የሰላም ጉዳይ መቼም የማይዋጥለት አሸባሪው ህወኃት ጦርነቱን የህዝብ ማዕበል በማሰለፍ ቢጀምረውም እንደ ህዝብ ጥቃት ሊያደርስ የመጣን ጠላት መመለስ የቻልነው እንደ ህዝብ አንድ መሆን መቻላችን መሆኑ ለማንም የተደበቀ አይደለም፡፡

አሸባሪው የጠላት ሃይል በትግራይ ክልል ተተኪ ትውልድ እንዳይኖር ዕድሜው 12 ዓመት ከሆነ ታዳጊ ህጻን ጀምሮ እስከ 64 ዓመት አዛውንት ድረስ በጦርነቱ ማሰለፍ ቢችልም ጀግናውን የጥምር ጦር ክንድ መቋቋም አቅቶት፣ መግቢያና መውጫው ተዘግቶበት ጭንቅ ውስጥ ገብቷል፡፡

ኢትዮጵያን ማፍረስና ምስራቅ አፍሪካን የትርምስ ማዕከል በማድረግ ልፍስፍስና ተገዢ መንግስት መፍጠር ዓላማ አድርጎ የተነሳው የውጭ ሃይል አሸባሪውን ትህነግን እንደመሳሪያ በመጠቀም የትርምስ ቀጠና ለመፍጠር እየሰራ መሆኑ ግልጽ ማሳያዎችን መጠቀስ ይቻላል፡፡ አሸባሪው ትህነግም በሰራዊታችን በኩል እየደረሰበት ያለውን እርምጃ መቋቋም ተስኖት እንደለመደው የድረሱልኝ ተማጽኖውም አውሮፓ ባስቀመጣቸው ወኪሎቹ በኩል እያስተጋባ ይገኛል፣አድማጭ ባያገኝም፡፡

ፀረ-ኢትዮጵያ አስተሳሰቡ ከጥንት ከድርጅቱ ምስረታ ጀምሮ አብሮት እያደገ የመጣው ትህነግ አሁን ደግሞ የኢትዮጵያ አልንበረከክም ባይነት ካሳሰባቸው ሃይሎች ጋር በመሆን ከዲፕሎማሲ ጦርነት ባሻገር ልዩ ልዩ ጫናዎችን ለመፍጠር እየተንቀሳቀሱ ይገኛል፡፡ እኛ ኢትዮጵያውያን ብሔራዊ ክብራችንን በጥቅም አሳልፎ የሚሸጥ ህሊና የለንም፡፡

ዛሬ የምንከፍለው መስዋዕትነት ነገ ሉዓላዊነቷ የተከበረችና ለማንም የማታጎነበስ አገር እንድትኖረን መሰረት ይሆናልና ዛሬም እንደጥንቱ ለአገር ክብር የምንዋደቅበት ወሳኝ ምዕራፍ ላይ እንገኛለን፡፡ምክንያቱም ነጻነት ያለ መስዋዕትነት ሊገኝ አይችልምና፡፡

ኢትዮጵያዊያን አሸባሪውን የትህነግ ቡድን እስከወዲያኛው እንዳይመለስ አድርገው ለመሸኘት ግብግብ ውስጥ ገብተዋል፡፡ ሰራዊታችንም በጠላት ሃይል ላይ ፈርጣማ ክንዱን እያሳረፈ መተኪያ ለሌላት ውድ አገሩ ህይወቱን እየገበረ ይገኛል፡፡ የጀመርነው ትግል ዳር እስኪደርስ ድረስ ሁሉም በጀመረው አግባብ ድጋፉን አጠናክሮ መቀጠል ይኖርበታል።

ሠራዊታችን ዛሬም ቢሆን አሸባሪውን ትህነግ ለአንዴና ለመጨረሻ ጌዜ ለማስወገድ እና እየተከተለ ያለው የእብሪት መንገድ በኢትዮጵያና ህዝቦቿ ላይ ምንም ዓይነት ቦታ እንደማይኖረው በሚገባው ቋንቋ ለማስረዳት በጽናት እየታገለ ይገኛል፡፡ በእስካሁኑ እንቅስቃሴውም በጠላት ላይ እያስመዘገበው ያለው ስኬት ከፍ ያለ ነው።

መላው ኢትዮጵያዊያን ሊያውቁት የሚገባው ጉዳይ ቢኖር ጠላት ተሸንፎ ወደተመኛት ሲዖል እንደሚሄድ ለአፍታም መጠራጠር አያስፈልግም፡፡ ከጠላት ጋር የጀመርነው ትግል በድል ለመቋጨት በፅናት እና በኢትዮጵያዊነት ወኔ ዛሬም እንደትናንቱ አንድ ሆነን መነሳት ይገባናል። የትግሉ መጨረሻ ግን ለኢትዮጵያዊን የአዲስ ምዕራፍ ጅማሬ ማብሰሪያ ይሆናል፡፡ የሕዝባችን የዘመናት እንባ በጀግኖች ትግልና መስዋዕትነት ይታበሳል፡፡ በኢትዮጵያ ሰማይ ላይ የሰላም አየር ይነፍሳል፡፡ ጠላት በተራው አንገቱን ይደፋል፡፡ የኢትዮጵያም ብልጽግና በህዝቦቿ መስዋዕትነት ይረጋገጣል፡፡

prosperity

ሁሌም የትም ከጀግናው የሀገር መከላከያ ሰራዊት ጎን መሰለፍ ክብርም ኩራትም ነው።

ሁሌም፤ የትም ከጀግናው የሀገር መከላከያ ጎን መሰለፍ ክብርም፤ ኩራትም ነው !!

መከላከያ ሰራዊታችንን በሞራልም በማቴሪያልም መደገፍ፤ አሸባሪው ህወሃት ከላኪና ተላላኪዎቹ ጋር የከፈተብንን ጥቃት ለመመከት ብቻ ታሳቢ ተደርጎ የሚሰራ አይደለም።

የውስጥ አንድነታችንን ይበልጥ አጠናክረን የጀመርነውን የብልፅግና ጉዞ ዳር ካላደረስን በድህነታችን ታከው ጦራቸውን የሚወረውሩብንም ወደ ፊትም መቀጠላቸው አይቀርም።

ኢትዮጵያውን የሰላም ጊዜ ወዛደር፤ የጦርነት ጊዜ ወታደር ሆነው ልማታቸውንና ሰላማቸውን መሳ ለመሳ ማስኬዱን ቢያውቁበትም እንኳንስ በጦርነት ላይ ሆነን በሰላሙ ጊዜም ቢሆን ጀግናውን መከላከያ ሰራዊታችን ሁለንተናዊ ድጋፍ በማድረግ ታፍራና ተከብራ የኖረችውን ኢትዮጵያን ማስቀጠል የኛ ትውልድ ታሪካዊ ሀገራዊ ሀላፊነት ነው።

ለውድ ሀገሩና ለወገኑ የህይወት መስዋዕትነት እየከፈለ ለሚገኘው ለጀግናው መከላከያ ሰራዊታችን ምንም ብናደርግለት ያንስበታል እንጂ አይበዛበትም። በመሆኑም ህይወታቸውን ሰውተው ኢትዮጵያን ከፍ ለማድረግ የተቃጣብንን ጦርነት በጀግንነት እየመከቱ ደማቅ ታሪክ እየፃፍ ያሉ ጀግኖችን የዕድሜና የጤና ሁኔታ ያልገደበው በመቀላቀል የዚህ ደማቅ ታሪክ አካል መሆን ያኮራልም ያስከብራልም።

ደም በመለገስ፣ ስንቅ በማዘጋጀት፣ ግምባር ድረስ ሄዶ ወይም በአገኘው አጋጣሚ ሞራል በመስጠት፣ የሚዋደቁላትን ሀገር ለማበልፀግ በተሰማሩበት ሁሉ ጠንክሮ መስራትም ከእያንዳንዳችን ይጠበቃል።

በሚዲያና በሰፈር በሬ ወለደ ወሬ በማውራት የመከላከያን ስም የሚያጠፉትን በመታገል መከላከያ ዳርድንበሩን ሲጠብቅ፤ የአካባቢን ሰላምና ፀጥታ በንቃት በመጠበቅ ለጀግኖቻችን አለኝታነታችንን በማሳየት ሀገራዊና ታሪካዊ ሀላፊነትና ግዴታችንን ሁላችንም ሁሌም፣ የትም እንወጣ።

ሕዝባዊ በዓሎቻችን ለአብሮነታችን!

በማራኪ አያሌው

የጊዜ ዑደትን ጠብቀው ወቅቶች ሲፈራራቁ የየራሳቸው ልዩ ውበት አላቸው፡፡ ጸደይ፤ መኸር፤ በልግም ሆነ የክረምት ወቅትና ወራቶች የተለያዩ ክዋኔዎች ጋር ተያይዘው የሚታወሱና የሚናፈቁ ናቸው፡፡ ተፈጥሮ ሆነና አንዳንዶቹ ወቅቶችና ወራቶችማ ሳንጠግባቸው ሽው እልም ይላሉ፡፡

ክረምቱ ተጋምሶ፤ ምድሪቱ አረንጓዴ ለብሳ አዲሱ አመት ሲቃረብ ደግሞ ስሜቱ ልዩ ነው፡፡ ይህ ወቅት በተለያዩ አካባቢዎች ከየማህበረሰቡ ወግ፤ ባህል እና እሴት የሚቀዱ ሕዝባዊ በዓላቶች ተከታትለው የሚከበሩበት ነው፡፡ የቡሔ፤ ሆያሆየ፤ ጎቤ (በኦሮሚያ የተለያዩ

አካባቢዎች እስከ መስቀል ድረስ የሚዘልቅ የወንዶች ጨወታ) ከወቅቱ ድምቀቶች መካከል ጥቂቶች ናቸው፡፡

በራያ ቆቦ ሶለል፣ በወልድያ አካባቢ ሶለልና አሸንድዬ፣ በላስታ ላልይበላና ሌሎች አካባቢዎች አሸንድዬና ሻደይ፣ እንዲሁም በዋግ ኽምራ ሻደይ በመባል የሚታወቀው በዓል ደግሞ ሌላኛው የወርሓ ነሐሴ ተጠባቂና ተናፋቂ ሁነት ነው፡፡

በዚህ ወቅት በባህል አልባሳትና ጌጣጌጦች የተዋቡ እንስቶች በአረንጓዴው መስክ ላይ ተሰብስበው ሲጫወቱና የክብረ በዓሉን ዜማዎች ሲያዜሙ በዓይነ-ሕሊናው ውልብ የማይልበት ያለ አይመስለኝም፡፡ ልጃገረዶች በተስራቅራቂ ድምጽ ሲያዜሙ ለሌላውም የበዓሉን ስሜት የማጋባት አንዳች ሓይል አላቸው፡፡

ይሁንና እንዲህ ያሉ በዓላት ከአካባቢው ማህበረሰብ በዘለለ በሌሎች ቦታዎች ሲከበሩ እምብዛም አይስተዋልም፡፡

በርግጥ ኢትዮጵያውያን ሃይማኖታዊና ሀገራዊ ክብረ በዓላትን በአንድነት የማክበር ባህል አለን፡፡ በተለያዩ አካባቢዎች የሚከበሩ ሕዝባዊ በዓላት አብሮ በማክበር ረገድ ግን ትኩረት የተሰጠው አይደለም፡፡ እነዚህን ህዝባዊ በዓላትን በጋራ ሆኖ ማክበር እርስ በርስ እንድንተዋወቅና አንዱ የአንዱን ባህል፤ ወግ እና አኗኗር እንዲረዳ እድል ይሰጣል፡፡

ይህ ደግሞ ወንድማማችነትን/እህትማማችነትን ያጠናክራል፡፡

እናም ዘንድሮውን የሻደይ፤ ሶለልና አሸንድዬ ክብረ በዓላትን ከሩቅ ሆኖ በማመተርና በመጎምዠት ሳይሆን አብሮ መሳተፍ ያስፈልጋል፡፡ ምክያቱም ጨምበላላ፤ ኢሬቻ፤ ጊፋታ፣ ሸዋሊ፣ ሻደይም ሆነ ሌሎች በዓሎች የጋራ ትውፊቶቻችን፤ የጋራ ሃብቶቻችን ናቸው፡፡ በዓሎቹን በጋራ ስናከብር እኛም አብረን እንከብራለን፡፡

የአባቶችን ህልም እና ፍላጎት እውን በማድረግ ሀገርን በፀና መሰረት ላይ ማቆም የዚህ ትውልድ ሃላፊነት ነው – ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አህመድ

የአባቶችን ህልም እና ፍላጎት እውን በማድረግ ሀገርን በፀና መሰረት ላይ ማቆም የዚህ ትውልድ ሃላፊነት ነው – ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አህመድ

የአባቶችን ህልም እና ፍላጎት እውን በማድረግ ሀገርን በፀና መሰረት ላይ ማቆም የዚህ ትውልድ ሃላፊነት ነው ሲሉ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አህመድ ገለፁ።

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድን ጨምሮ ከፍተኛ የመንግስት የስራ ኃላፊዎች በተገኙበት የህዳሴ ግድብ 2ኛ ተርባይን ኃይል ማመንጨት መጀመር ማብሰሪያ ሥነ ስርአት እየተካሄደ ይገኛል፡፡

ጠቅላይ ሚኒስትሩ የታላቁን የኢትዮጵያ ሕዳሴ ግድብ 2ኛ ተርባይን የኤሌክትሪክ ኃይል ማመንጨት በይፋ መበሰርን አስመልክቶ ባስተላለፉት መልዕክት የህዳሴ ግድብ እውን መሆን በርካታ ዋጋ ተከፍሎ ተረት የነበረው ግድብ ታሪክ ማድረግ መቻሉ ጠቅሰዋል።

ትውልዱ አባቶች ያሰቡትን ህልም እና ፍላጎት እውን በማድረግ ሀገርን በፀና መሰረት ላይ የማቆም ሃላፊነት እንዳለበት አስገንዝበዋል።

በታሪክ ውስጥ ማለፍ እና ታሪክ መስራት ይለያያል ያሉት ጠቅላይ ሚኒስትሩ፤ “በታሪክ ውስጥ ማለፍ እድል፤ ታሪክ መስራት ደግሞ ድል ነው” ብለዋል።

ቀደም ባሉ ግዜያት የቁጭት ዘፈኖችና ተረቶች ሲያስተናግድ የነበረው የህዳሴ ግድብ እውን ሆኖ ወደ ታሪክነት ተቀይሯል ሲሉም ነው ጠቅላይ ሚኒስትሩ የገለጹት።

በዛሬው እለት ስራ የሚጀምረው ዩኒት ዘጠኝ ሲሆን፥ 270 ሜጋ ዋት ሃይል የማመንጨት አቅም እንዳለው ተጠቅሷል፡፡
ባለፈው የካቲት ወር ላይ 270 ሜጋ ዋት የሚያመነጨው ዩኒት10 ኃይል ማመንጨት መጀመሩ ይታወሳል።

ይህን ተከትሎም ታላቁ የኢትዮጵያ ህዳሴ ግድብ የዛሬውን ጨምሮ በአጠቃላይ 540 ሜጋዋት የኤሌክትሪክ ኃይል ማመንጨት እንደሚችል ተጠቁሟል፡፡

ቃላችንን አላጓደልንም!!


በማራኪ አያሌው

ከአራት ዓመታት በፊት ሀገራዊ ለውጡ ሲበሰር የህዝባችን የለውጡን ፍሬዎች የማጣጣም ተስፋ ላቅ ያለ ነበር፡፡ የለውጥ አመራሩም ይህን የሕዝቡን ፍላጎት ለማርካት ሲረባረብ ቆይቷል፡፡ ህዝባችን በለውጡ ዘመን የእንጦጦ ከፍታ ከጫካነት ወደ ውብ ተፈጥሯዊ መዝናኛነት ሲቀየር ተመልክቷል፡፡ የቤተ መንግስት ቅጥር ጊቢ ለምቶና ተውቦ ሲበረከትለት፤ ጎርጎራና ወንጪ የልማቱ ተቋዳሽ ሰሆኑ አይቷል፡፡

የተቋማትና የምጣኔ ሃብት ሪፎርምን፣ የዜጎችና የሀገር ክብርና ፍቅር ከፍ ማለትን፣ ሳይፈልግ የተጫነበት የልዩነት ትርክት በአዲስ የአብሮነትና የወንድማማችነት ትርክት መቀየርን ሲመለከት ለሀገር አንድነት መሰረት እየተጣለ በመሆኑ ተስፋው ያልለመለመ ኢትዮጵያዊና የኢትዮጵያ ወዳጅ የለም፡፡ ዓለም አቀፉ ማህበረሰብም በለውጡ ላደረጉት አበርክቶ ለጠቅላይ ሚኒስትር ዶ/ር አብይ አህመድ የሰላም ኖቤል ሽልማትን በማበርከት አድናቆቱን ቸሯል፡፡

ከለውጡ በተቃራኒ የነበሩት አካላት ግን እጃቸውን አጣጥፈው አልተቀመጡም፡፡ የሕዝቡን ፍላጎትና ውሳኔ አሜን ብለው መቀበል አልፈለጉም፡፡ አንድም በፍርሃት፤ ሁለትም እኔ ከሞትኩ … እንደሚሉት ሆኖባቸው ከውጪ ሃይሎች ጋር ጭምር ተቀናጅተው በሚለኩሱት እሳት ብዙ መከራ አስተናግደናል፡፡ የዜጎች ሞት፤ መፈናቀል፤ ግጭት፤ የመሰረተ ልማት ውድመት፣ ወዘተ … ጉዟችንን አድካሚ፤ ድላችንንም በፈተና የታጀበ እንዲሆን አድርገውታል፡፡

አንዳንድ የውጪ ሃይሎች እነሱ በቀየሱልን መንገድ ብቻ እንድንራመድ በየምዕራፉ የነበረው ጉተታ አይዘነጋም፡፡ በታላቁ የሕዳሴ ግድብ፤ በምርጫና በተለያዩ ጉዳዮች “እኛ ካልወሰንላችሁ” የሚለው መረን የለቀቀ ጣልቃ ገብነታቸው ከምኞት ባያልፍም ዋጋ አስፍሎናል፡፡ እኛ ግን በየግንባሩ የተከፈተብንን ዘመቻ በጋራ በመመከት እጣ ፈንታችን እንደ ሀገር በአንድ ላይ የተሰናሰለ በቀላሉ የማንሰበርና የማንበታተን ጠንካራ ሕዝብ መሆናችንን በዓለም አደባባይ አስመስክረናል፡፡

በነዚህ ዓመታት በአንድ በኩል ችግሮችን በመቀልበስና የሀገር አንድነትን በማስጠበቅ በሌላ በኩል ልማትን በማፋጠን የለውጥ አመራሩ ቃሉን ሳያጓድል ቀጥሏል፡፡ እንደ ሀገር ያነገብነው ራዕይ እና ሕዝቡ የሰጠን አደራ ከሚፈታተኑን ችግሮች በላይ ናቸውና የብልፅግና ጉዟችን ከስኬት ማማ ሳይደርስ አይቆምም፡፡ የሰፊውን ሕዝብና የሀገርን ተስፋ ያለመለሙትን የለውጡን መልካም ወረቶች እያካበትን የፍርሃት ቆፈን ለብሶ ከፊታችን የቆመውን ፀረ ለውጥ ሃይል አልፈንው እንሄዳለን፡፡

Prosperityparty #prosperity

Design a site like this with WordPress.com
Get started