የመታወቂያ አገልግሎት

ለበርካታ አመታት የጤና እክል ገጥሟቸው አልጋ ላይ ቢወድቁም በቤት ለቤት የመታወቂያ ዕድሳት አገልግሎት በማግኘታቸው ደስተኛ መሆናቸውን ነዋሪዎች ገለፁ።

የኮ/ቀ/ክ/ከተማ ወረዳ 06 ወሳኝ ኩነት እና የነዋሪዎች አገልግሎት ምዝገባ እና መረጃ ቅርንጫፍ ጽ/ቤት የቤት ለቤት የመታወቂያ እድሳት አገልግሎት በተለያዩ ቀጠናዎች በመዘዋወር በዛሬው ዕለት ሰጥቷል።

በዛሬው እለት በወረዳው ቀጠና 5 ነዋሪ የሆኑት አቶ ስዩም በለጠ በህመም ምክንያት መጥተው መገልገል ስላልቻሉ በቤታቸው በመሄድ አገልግሎቱ ተሰጥተዋቸዋል።በተመሳሳይ መልኩ በቀጠና 3 የወ/ሮ ሁሩሜ ጂዳ በህመም ምክንያት መጥተው መገልገል ስላልቻሉ የቤት ለቤት መታወቂያ አገልግሎት አግኝተዋል።

ግለሰቦቹ ለበርካታ አመታት የጤና እክል ገጥሟቸው አልጋ ላይ ቢወድቁም በቤት ለቤት የመታወቂያ ዕድሳት አገልግሎት በማግኘታቸው ደስተኛ መሆናቸውን ገልፀዋል።

የቤት ለቤት መታወቂያ አገልግሎት በህመም እና በእርጅና ምክንያት መጥተው ለመገልገል ለሚቸገሩ የሚሰጥ ሲሆን ተገልጋዩ ያለበትን ሁኔታ ባለሙያዎች ወርደው በማየት በመመሪያ መሰረት አስፈላጊውን አገልግሎት የሚሰጡበት ነው።

የፅ/ቤቱ ኃላፊ ወ/ሮ ዲቦራ በቀለ በፅ/ቤቱ መጥተው ለመገልገል ለሚቸገሩ ነዋሪዎች አገልግሎቱን ለመስጠት ዝግጁ መሆናቸውን ገልፀዋል።
ለበለጠ መረጃ የማህበራዊ ትስስር ገጾቻችንን ይጎብኙ
https://twitter.com/kolfeS
https://t.me/kolfeworeda6
https://instagram.com/kolfewereda6?igshid=YmMyMTA2M2YKolfe Woreda 6 Prosperity Party -ብልጽግናpp
tiktok.com/@kkw6_prosperity
https://youtu.be/kUyWNtl8qE8
https://www.facebook.com/kw6pp

የብልፅግና ፓርቲ አዲስ አበባ ቅርንጫፍ ጽ/ቤት ኃላፊ አቶ ሞገስ ባልቻ በከተማችን እየተሰሩ ባሉ ስራዎች እና በወቅታዊ ጉዳዮች ዙሪያ ከክ/ከተማ እና ከወረዳ አመራሮች ጋር በቪዲዮ ኮንፈረንስ ተወያዩ

አቶ ሞገስ ባልቻ በውይይቱ ላይ እንደተናገሩት ብልፅግና ፓርቲ ከለውጡ ጀምሮ ያጋጠሙ ፈተናዎችን ወደ ድል እየቀየረ መምጣቱን አውስተው እህትማማችነትንና ወንድማማችነትን በማጠናከር የብልፅግናችን ስኬታማነት እናጎለብታለን ብለዋል።

ሁሉም ብሔር ብሔረሰቦች እኩል ተሳታፊና ተጠቃሚ የሚሆኑበት ስርዓት በመዘርጋቱ ህብረብሔራዊ አንድነትን የሚያጠናክሩ ተስፋ ሰጪ ስኬቶች መመዝገባቸውን የገለፁት ኃላፊው በአዲስ አበባ በአጭር ጊዜ ውስጥ ተጀምረው እየተጠናቀቁ ያሉ ፕሮጀክቶች ለዚሁ ማሳያ መሆናቸውን አስረድተዋል።

በብልፅግና መርህ ላይ በመቆም ፅንፈኝነትን ከህዝቡ ጋር በመታገል የከተማችን አስተማማኝ ሰላም ማስቀጠልና ልማታችንን ማፋጠን ይገባል ያሉት አቶ ሞገስ በቀጣይ ቀናት ከተለያዩ የህብረተሰብ ክፍሎች ጋር ህዝባዊ ውይይቶች እንደሚኖሩ ጠቁመዋል።

“ዛሬ የምናያቸውና የምንረማመድባቸው መንገዶች በአንድ ወቅት ጢሻ የነበሩና በፊት ቀደሞች መሥመር የወጣላቸው ናቸው። ዛሬ የሰለጠኑ ሀገሮች የሥልጣኔ ከፍታ ላይ የደረሱት በአንድ ወቅት ፊት አውራሪዎቻቸው በመከራ ውስጥ አልፈው፣ ችግር እና ፈተናውን ተሻግረው መሠረት ስላኖሩላቸው እንጂ አዲስ ተዓምር ተፈጥሮላቸው አይደለም።

ድኅነት፣ መታደስና ብልጽግና የሚመጣው ፊት ቀዳሚዎች ችግርና መከራውን ተጋፍጠው መንገድ ማስመር ሲችሉ ብቻ ነው። እኛ የዛሬው ትውልዶች ለሀገራችን ፊት ቀዳሚዎቿ እንደሆንን ማመን ይገባናል።

እኛ መከራዋን ሳንቀበል ለኢትዮጵያችን ምቾት፣ ዝቅታውን ሳናይ ለሀገራችን ከፍታ፣ ጭለማውን ሳንጎበኝ ለልጅ ልጆቻችን ብርሃን እንደማይመጣ ማወቅ አለብን።”

የብልፅግና ፓርቲ ፕሬዝዳንት ዶ/ር ዐቢይ አህመድ

በአዋሽ አርባ ዛሬ የተመለከትነው የተቀናጀ የውጊያ ልምምድ ኢትዮጵያ ጦርነትን የሚያስቀር ሀይል መገንባቷን ነው።

በውጊያ ልምምዱ አየር ሀይል ፣ ከባድ መሳሪያ ፣ልዩ ሀይል እና እግረኛ ተቀናጅቶ ውጊያን በአጭር የሚያስቀርባቸውን መንገዶች ተመልክተናል ።

በየቀኑ አይናችንን ከምንፈልገው ህልም እና ተግባራችን እንድናነሳ የሚሹ ሀይሎች ስላሉ የጦር መኮንኖች ዋና ተግባር የሚሆነው ጦርነትን የሚያስቀር ሀይል መገንባት ነው።

Shakalli waraanaa qindaa’aa har’a Awaash Arbaatti ilaalle Itoophiyaan humna waraana hambisuu danda’u ijaaruusheeti.

Shaakala waraanaa kana irratti Humni Qilleensaa, meeshaa gurguddaan, humni addaafi warri lafoon qindaa’anii yeroo gabaabaa keessatti akkaataa ittiin waraana hambisan ilaalleerra.

Humnoonni guyya guyyaan ija keenya waan barbaannurra akka kaafnu barbaadan waan jiraniif hojiin guddaan qondaaltota waraanaa humna waraana hambisu ijaaruudha.

ስልጠና ተሰጠ

ጠንካራ ፓርቲ ለጠንካራ መንግስት በሚል መሪ ቃል ለወረዳው ብልፅግና ፓርቲ የቢሮ መሰረታዊ ፓርቲና ህዋስ አመራሮች ስልጠና ተሰጠ።

ጥር 20/2015 ዓ.ም የወረዳው ብልፅግና ፓርቲ ፖለቲካ ዘርፍ ኃላፊ ወ/ሮ ፍቅርተ እሸቱ በወረዳው ለሚገኙ የብልፅግና ፓርቲ የቢሮ መሠረታዊ ፓርቲና ህዋስ አመራሮች ፖርቲውን በማጠናከር ጠንካራ መንግስት መፍጠር በሚቻልበት አግባብ ስልጠናውን ሰጥተዋል።

ኃላፊዋ ሌብነትን በመታገል በአገልግሎት አሰጣጥ የረካ ማህበረሰብን የረካ አገልጋይ መፍጠር በሚቻልበት ጉዳይ ላይም ከአመራሮቹ ጋር ውይይት አድርገዋል።

አመራሮቹ ፓርቲን በማጠናከር ጠንካራ መንግስት ለመፍጠር በሚደረገው ጉዞ ላይ ሁለንተናዊ ተሳትፎ እያደረጉና ይህንኑ ለማስቀጠል ያላቸውን ዝግጁነት የገለፁ ሲሆን ሌብነት የፓርቲው ቀይ መስመር መሆኑን በመረዳት አምርረው እንደሚታገሉ ገልፀዋል።

ኃላፊዋ በወቅታዊ ሀገራችን ጉዳዮች ዙሪያም ከአመራሩና ከአባሉ ምን ይጠበቃል በሚልም ከአመራሮቹ ጋር ምክክር አድርገዋል።

በ2015 በጀት አመት የ 6 ወር አፈፃም በክ/ከተማው ከሚገኙ ወረዳዎች 1ኛ ደረጃ ይዘን አጠናቀናልን እንኳን ደስ አለን!🏆🏆🏆🏆
አቶ አበበ ዘላለም
የኮ/ቀ/ክ/ከተማ ወረዳ 06 ም/ስራ አስፈፃሚ እና የስራ/ኢ/ኢ/ል/ፅ/ቤት ኃላፊ

ባለፉት ስድስት ወራት የነዋሪዎችን ጥያቄ ለመፍታት ብሎም ተቋማዊ አሰራር ለመገንባት ያለ መታከት አጠቃላይ አመራሩን፣የፅ/ቤቱን ቡድን መሪዎች፣ባለሙያዎች እና ነዋሪውን ያሳተፈ ርብርብ አድርገናል።

በ2015 በጀት አመት በ6 ወር አፈፃም በክ/ከተማው ከሚገኙ ወረዳዎች 1ኛ ደረጃ ይዘን የማጠናቀቃችን ዋነኛ ምክንያት በቅንጅት መስራታችንና ያለንን ሙሉ አቅም መጠቀማችን ነውና እንኳን ደስ አለን እንኳን ደስ አላችሁ።

በቀጣይ ይህንኑ ውጤት በማስቀጠል የነዋሪውን ተጠቃሚነት ከፍ ለማድረግ የምንሰራ መሆናችንን ስገልፅ በታላቅ ደስታ ነው!

አቶ አበበ ዘላለም
የኮ/ቀ/ክ/ከተማ ወረዳ 06 ም/ስራ አስፈፃሚ እና የስራ/ኢ/ኢ/ል/ፅ/ቤት ኃላፊ

ለበለጠ መረጃ የማህበራዊ ትስስር ገጾቻችንን ይጎብኙ
https://twitter.com/kolfeS
https://t.me/kolfeworeda6
https://instagram.com/kolfewereda6?igshid=YmMyMTA2M2YKolfe Woreda 6 Prosperity Party -ብልጽግናpp
tiktok.com/@kkw6_prosperity
https://youtu.be/kUyWNtl8qE8
https://www.facebook.com/kw6pp

ከንቲባ ወ/ሮ አዳነች አቤቤ በዛሬው እለት በለሚ ኩራ ክ/ከተማ የቅዱስ ጊዩርጊስ የስፖርት ክለብ ደጋፊዎች ማህበር የረጅም ጊዜ ጥያቄ የነበረውን የስፖርት ማዘውተርያ 10 ሺህ ካ.ሜ ቦታ ርክክብ አድርገዋል፡፡

እንደሚታወቀው ከንቲባ ወ/ሮ አዳነች አቤቤ ከቅዱስ ጊዮርጊስ እና ኢትዮጵያ ቡና ስፖርት ክለብ ደጋፊዎች ጋር ውይይት ባካሄዱበት ወቅት ደጋፊዎቹ ካነሷቸው በርካታ ጥያቄዎች መሀከል አንደኛው የስፖርት ማዘውተርያ ስፍራዎችን የማስፋፋት ጥያቄ ነው፡፡

እነሆ በዛሬው እለት ከንቲባ ወ/ሮ አዳነች አቤቤ የወጣቶቹ ጥያቄ አንዱ የሆነው የቅዱስ ጊዮርጊስ ስፖርት ክለብ ደጋፊዎች ማህበር የስፖርት ማዘውተርያ ስፍራ በቦታው ላይ የነበሩ የተለያዩ ህገወጥ ደላሎችንና የይገባኛል ጥያቄዎችን በመፍታት ለክለቡ ደጋፊዎች ማህበር በቦታው በመገኘት አስረክበዋል፡፡

በዚሁ ወቅት ከንቲባ አዳነች እንደተናገሩት ይህንን የስፖርት ማዘውተርያ ስፍራ ቦታ ብቻ ሳይሆን ሀገርንም የምንገነባው ተባብረን ነው ያሉ ሲሆን ልክ እንደዚሁ ቦታ ሁሉ በከተማው የተለያዩ የልማት ስራዎቻችን ከህገወጥ ደላሎች ጋር ትንቅንቅ በማድረግ የልማት እቅፋቶችን እየተጋፈጥን ነው ስራዎችን እየሰራን ያለነው ብለዋል፡፡

በመሆኑም ህብረተሰቡ የተጀመሩ የልማት ስራዎች ተጠናክረው እንዲቀጥሉ በየአካባቢው ለልማት እንቅፋት የሚሆኑ ህገወጥ እቅስቃሴዎችን በመግታት ሚናውን እንዲወጣ ጥሪ አቅርበዋል፡፡

ዛሬ ርክክብ የተደረገበትም ቦታም በፍጥነት ወደ ልማት እንዲገባ አቅጣጫ ሰጥተዋል የክለቡም ቦርድ በፍጥነት ግንባታውን እንደሚያስጀምር ቃል ገብቷል።

የሌማት ትሩፋት

በስንዴ፣በአቮካዶ፣በፓፓያ፣በሙዝ፣በቡና በአረንጓዴ አሻራ ያገኘነው ልምድ ቀላል አይደለም።

በግብርና ዘርፍ የለውጥ ትራንስፎርሜሽን ለማምጣት እቅድ ነድፈን ጉዟችንን ሀ ብለን ከጀመርንበት እለት ጀምሮ ኢትዮጵያ ያላትን እምቅ ሀብት ተረድተናል።

ይሄም ለትልቅ ተስፋ እና ራእይ ያነሳሳን ሲሆን እቅዶቻችን በትንሽ ድካም ፍሬ ሊያፈሩ እንደሚችሉ እና ህዝባችንም ለልማት ስራዎች ልበ ቀና መሆኑ በሁሉም አካባቢዎች የተገነዘብነው ሀቅ ነው።

እንደ ሀገር በክቡር ጠቅላይ ሚኒስትራችን አማካይነት በአርባ ምንጭ ከተማ ይፋ የተደረገው የሌማት ትሩፋት የልማት ዘመቻ በህዝባችን እንደሚሳካ ተማምነን የጀመርነው እንቅስቃሴ ነው።

የሌማት ትሩፋት ትኩረቱ የዶሮ፣የወተት፣የእንቁላል እና የስጋ ምርቶች በስፋት በሀገራችን እንዲኖሩ ማስቻል እና ወተት መጠጣት፣ዶሮ መብላት፣እንቁላል መመገብ ለህዝባችን የቅንጦት ጉዳይ ሳይሆን እለት በእለት በቀላሉ የሚገኙ የምግብ አማራጮች እንዲሆኑ ማስቻል ነው።

ክቡር የፓርቲያችን ፕሬዝዳንት ዶ/ር ዐቢይ አህመድ በአንድ ወቅት ከወጣቶች ጋር በነበራቸው ውይይት እንደተናገሩት የምግብ ዋስትናቸውን ባረጋገጡ ሀገራት የእንሰሳት ምርት ላይ ትኩረት አድርገው መስራታቸው የግብርናቸው ትሩፋት እንዲያድግ እንዳደረገው ገልፀዋል።

ለአብነት ያህልም ዶሮ በተቀረው አለም ላይ የቅንጦት ምግብ ሳይሆን እጅግ ርካሽና እሴት ተጨምሮበት ከአንድ ዶላር በታች የሚሸጥ ምግብ እንደሆነ ተናግረዋል።

ይህ ባደጉት ሀገራት ብቻ ሳይሆን በበርካታ አፍሪካ ሀገራትም ጭምር የሚታይ እውነታ ነው።በመሆኑም በሀገራችን ይህ ልምምድ እንዲዳብር የተዳቀሉ ምርጥ ዝርያዎችን በማስፋፋት፣የእንቁላል መፈልፈያ ቴክኖሎጂዎችን በመጠቀም፣ዘርፉ በእውቀት እንዲመራ በማድረግ አመርቂ ውጤት ማስመዝገብ ይኖርብናል።

በተመሳሳይ በስጋ፣በወተት እና በማር ይህን መሰል ልምምዶች በስፋት ያስፈልጉናል።ገበሬዎቻችን የሌማት ትሩፋት ዘመቻ መዳረሻ ግቡ ምን እንደሆነ ተረድተው የሚቀርቡ የቴክኖሎጂ ውጤቶች በቀናነት እንዲቀበሉ ከልማዳዊ አሰራር እንዲወጡ ማድረግ ያስፈልጋል።

Prosperity

በነብር ከተመሰለው የደቡብ ኮሪያውያን ብልጽግና ምን እንማር?

የገቡበት የመከራ ጥልቀት እንዲህ በቀላሉ አይገለፅም፡፡ ጀርባቸው ላይ ያላረፉ የመጥፎ ታሪከ አሻራዎች አልነበሩም፡፡ ድህነት፣ ረሀብ፣ ስደት፣ ጦርነት እና ግዞት ሁሉም በየፈርጁ ተፈራርቀው ተስፋ ቢስነት ውርሳቸው እንዲሆን አስቀያሚ ገፅታን አልብሰዋቸዋል፡፡

የሚመኩበት የተፈጥሮ ሀብት የሌላቸው፤ ያላቸውን በአግባቡ መጠቀም እንኳን እንዳይችሉ በግዞት ስር የወደቁ፤ የፖለቲካ ሽኩቻ ጥሪት አልባ አርጎ ለዘመናት የቀረፃቸው ሆነዋል፡፡ ታሪካቸው ላይ በበጎ እንኳን የሚከተብ የሚለቀም ጠፍቷል፡፡

ድልን እንዳይፅፉ ተንበርክከዋል፤ ጥጋብን እንዳይፅፉ ተርበዋል፤ ትውልድን እንዳያስቡ ያለው መክኗል፤ ሴቶች ተመርዘው ወንዶች በባርነት ስር ወድቀዋል፡፡ ታሪኩ ለማመን የሚከብድ ቢሆንም ከዛሬ 65 አመት በፊት የነበረ የዛሬዎቹ የደቡብ እና የሰሜን ኮሪያ ከፍቺ በፊት የተቋደሱት የጋራ ታሪክ ነው ! ባለቤቶች ደቡብ ኮሪያውያን!

በኮሪያውያን ታሪክ እኤአ ከ1910 እስከ 1945 ባሉት 35 አመታት በግዞት የነበሩበት የስብራት መጠን ሊጠገን የሚችል አይመስልም ነበር፡፡ የጃፓን ወረራ ተብሎ በተጠራው የያኔው ግፍ የደረሰባቸው የሰብአዊነት፤ የሞራል፤ የጦርነት ኪሳራ ቀላል አልነበረም፡፡ ከምንም በላይ ወረራው ትኩረቱ ኮሪያውያንን በሁለመና ማድቀቅ እና ማንበርከክ ስለነበር በጃፓን በኩል እጅግ የተጠና ስነልቦናዊ የማዳከም ስራ ይሰራባቸው ነበር።

በተለይም የካርታቸው ቅርፅ “ተዳክማ እግሯን ወደ ላይ ያደረገች ጥንቸል ይመስላል” በማለት ደካማ እና ሰነፍ ህዝቦቸ ናቸው የሚል ትርክት እንዲሰርፅ ለ3 አስርት አመታት ሰርተዋል። ከጊዜ በኋላም ነገሮች ተቀያይረው ጃፓን በሁለተኛው የአለም ጦርነት ተሸንፋ፤ ኮሪያም ከአንድ ወደ ሁለት ደቡብ እና ሰሜን ሆና ተሰንጥቃ በደካማ ጥንቸል ሲመሰል የኖረው ካርታ ቅርፁ ቢለወጥም በተለይም ደቡብ ኮሪያውያን ከደካማ እና ሰነፍ ጥንቸልነት ስነልቦና ለመላቀቅ ከብዷቸው ነበር፡፡

ነገር ግን ያንን የግዞት ስነልቦና ለመቀየር እና የአሸናፊነት ብሎም የድል አድራጊነትን ስነልቦናን ለመቀናጀት በጃፓን ጥንቸል ተደርጎ የተመሰለውን “የለም ስህተት ነው እኛ በደካማ ጥንቸል ሳይሆን በአሰፍሳፊ ነብር መመሰል የሚገባን ህዝቦች ነን” በሚል እሳቤ ተክተው ጉዞ ጀመሩ፡፡
ጥንቸልን በነብር የተካው የነፃነት ትርክትም ፍሬ እንዲያሳይ እና ለሀገር ግንባታ ጡብ መሆን እንዲችል ደቡብ ኮሪያውያን ራሳቸውን በአሰፍሳፊ ነብርነት ስነልቦና የቀረፁበት መንገድ እውነተኛ ፍሬ አፈራና በነብር እንጂ በጥንቸል ሊመሰሉ የማይገባቸው መሆኑን ማስመስከር ቻለ፡፡

የነብርን ድፍረት፤የአይኖቹን የትኩረት ብቃት፤የጥፍሮቹን ጉልበት፤የደፈጣ ጥበቡን ረቂቅነት እያስተዋሉ በአሸናፊነት ስነ-ልቦና ወደ ብልፅግና መገስገስ ጀመሩ፡፡ በአጭር ጊዜም ድካማቸው ፍሬ እያፈራ፤የነብርነት ትርክት ጥንቸሏን እየዋጣት፤ግዞት ማንነታቸውን የትላንት ታሪክ ትኩረታቸውን ያልሰረቃቸው በረሃን ወደ ገነት መቀየር የሚችል ትንታግ ሆነው ታዩ፡፡
ትላንት ይሄ ነው የምትለው መኩራሪያ ያልነበራት ደቡብ ኮሪያ ዛሬ በግንባር ቀደምነት የሚጠቀስ የኢኮኖሚ ባለቤት፤የቅንጦት ኑሮ ምሳሌ፤የፈጠራ ሰገነት፤የአለም ትልልቅ ካምፓኒዎች መፈልፈያ እና የብልፅግና ማሳያ መሆን ችላለች፡፡

የጥንቸልነትን ትርክት አራግፎ ነብርነትን ያስታጠቃቸው ስነልቦና መፈፀም፤ማሳካት፤መለወጥ፤ማደግ እንደሚችሉ ማሳያ ሆነ፡፡

አሁን ጥያቄው ኢትዮጵያን ማበልጸግ እንድንችል እኛስ ከዚህ ምን እንማር የሚለው ነው፡፡
መልሱ ቀላል ነው….

እኛ ኢትዮጵያውያን ከውጪ በመጣ ጠላት የታሪክ ትብታቦ ያልተዘወርን፤ የግዞት ቀንበር ያልተጫነብን፤ የአሸናፊነት ስነልቦና ዘወትር ያልተለየን ህዝቦች ነን፡፡ መሬታችን ለም እና ሰፊ፤ ህዝባችን እልፍ፤ተፈጥሯችን ባለ ብዙ በረከት፤ ነፃነታችን ሽንፈት አልባ የሆነ፤ ግምባራችን ላይ ድል የተፃፈ አሸናፊዎች ነን፡፡

ረሀብ ቢወረን በእጆቻችን ስንፍና፤ጥማት ቢያቃጥለን በማንቀላፋታችን፤ ስንዴ ቢሰፈርልን ትጋት በማጣታች እንጂ ወደ ብልፅግና ለመስፈንጠር ጥሪት አልባዎች ሆነን አይደለም፡፡

ያለንን ውድ ስጦታ መንዝረን ወደ ሀብትነት ቀይረን ዛሬ ብንነሳ ቁንጮ መሆን የምንችል፤ ብንሰራ እና ብንተጋ ተፈጥሮ ፊቷን የማታዞርብን፤ ከኋላ የሚጎትት የጭቆና ቀንበር የሌለብን፤ በህብረት ስንቆም አሸናፊዎች መሆን የምንችል እንደሆነ ጥርጥር የለውም፡፡

ኢትዮጵያን ለማበልፀግ የአሸናፊነት፤የፈፃሚነት፤የጨራሽነት፤የድል አድራጊነት፤የሰርቶ አሳይነት እና በህብረት ድል አድራጊነት ስነልቦናን አጎልብተን ወደ ብልፅግና ባቡር መሳፈር ይጠበቅብናል፡፡ እንንቃ! ትኩረታችን በከንቱ ሳይባክን፤አቅማችን ሳይዝል ታካችነት እና አሳባቢነትን ወደ ጎን ትተን ለታላቅ ሀገር ግንባታ እንሰለፍ፡፡

ሀገር አንድ በሆኑ ህዝቦች እንጂ በተከፋፈሉ አትገነባምና ህብረታችን ይጠንክር፤ሀገር በአሸናፊነት ስነልቦና እንጂ በሰበብ አብዢነት እሳቤ አትበለፅግምና ምክንያት ደርዳሪነትን እንተው፡፡ሀገር ለህዝቡ አንድ የውሀ ጉድጓድ መቆፈር በሚችል እንጂ በጎጥ እሳቤ ንትርክ ሲፈትል ውሎ በሚያድር መፍትሄ አልባ ፖለቲከኛ መገንባት አትችልምና የሴራ ፖለቲካን ገፍተን ወደ ሀሳብ እንመለስ፡፡ ድህነትን ስንረገም መዋልም ወደ ብልፅግና አያሻግርም እና ትኩረታችን ብልፅግና ይሁን፡፡

prosperity

የስንዴ ፍላጎትን በአገር ውስጥ የመሸፈን ግብግብ


ኢትዮጵያ የስንዴ ፍላጎቷን በአገር ውስጥ ምርት ለመሸፈን የምታደርገው ጥረት ትክክለኛ አቅጣጫ የተከተለና ለውጤት እያበቃን ስለመሆኑ በርካታ ማሳያዎችን መጥቀስ ይቻላል። ኢትዮጵያ ከውጭ የምታስገባውን ስንዴ በአገር ውስጥ ምርት ለመተካት በርካታ ሥራዎች እያከናወነች ትገኛለች።

ለዚህም ደግሞ የኩታ ገጠም የግብርና ሥራና የመስኖ ልማት ሥራዎች እየተካሄዱ በመሆናቸው አገሪቱ በትክክለኛ የግብርና አቅጣጫ ላይ መሆኗን የሚያሳይ ንቅናቄ መፍጠር ተችሏል፡፡

ኢትዮጵያ ለስንዴ ምርት የሚሆን ከፍተኛ የውኃና የመሬት አቅርቦት እንዳላት በዘርፉ የተሰማሩ ምሁራን ሲናገሩ ይደመጣል፤ይህንን ዕድል በአግባቡ ተጠቅሞ ከራስ ፍጆታ አልፎ ለውጭ ገበያ ለማቅረብ ጠቀሜታው ከፍ ያለ ነው፡፡

ጠ/ሚ ዶ/ር ዐብይ አህመድ ኢትዮጵያ የስንዴ ፍላጎቷን በአገር ውስጥ ምርት ለመሸፈን ብሎም ለውጭ ገበያ በማቅረብ የውጭ ምንዛሬን ለማግኘት እንዲቻል በየደረጃው የሚገኙ የፓርቲው አመራሮች ልዩ ትኩረት ሰጥተው ክትትል እንዲያደርጉ አቅጣጫ ከመስጠታቸው ባሻገር በተለያዩ አካባቢዎች በመንቀሳቀስ የደረሰበትን ደረጃ እየጎበኙ ይገኛሉ፡፡

አገሪቱ በስንዴ እርሻ ሥራ ላይ እያሳየች ያለውን ጥረት ማስፋት ከቻለች በአጭር ጊዜ ውስጥ ‘በምግብ ራስን መቻል’ የሚለውን ትልቅ እቅድ ማሳካት እንደሚቻል ከመጠቆሙም በላይ ለውጭ ንግድ የሚቀርቡ የግብርና ምርቶችም ሊኖሩ እንደሚችሉ ያሳዬ ነው።

መንግሥት አሁንም ለዘርፉ እድገት ትኩረት በመስጠት በተለይም ለአርሶ አደሩ በተመጣጣኝ ዋጋ እያቀረበ ያለው ማዳበሪያ ለዘርፉ የተሰጠውን ትኩረት ያሳዬ ነው፡፡

አርሶ አደሩ ትክክለኛውን ቴክኖሎጂ እንዲጠቀም በየዕለቱ ድጋፍ ማድረግ፤ ተመራማሪዎች ከአከባቢው ሥነ-ምህዳር ጋር ተስማሚ የሆኑ መፍትሄዎችን ማአርሶ አደሩ ትክክለኛውን ቴክኖሎጂ እንዲጠቀም በየዕለቱ ድጋፍ ማድረግ፤ ተመራማሪዎች ከአከባቢው ሥነ-ምህዳር ጋር ተስማሚ የሆኑ መፍትሄዎች ማስቀመጥ ይገባል።

በስንዴ እርሻ የተሰማሩ አርሶ አደሮችም ሆኑ ባለሃብቶች ከመንግሥትና ከግብርና ባለሙያዎች የሚቀርቡላቸውን ምክረ ሃሳቦች በአግባቡ ተግባራዊ በማድረግ ምርታቸውን ማስፋት ይኖርባቸዋል። በስንዴ ምርት ላይ ያለውን የትኩረት ተደራሽነት በማስፋት የዘርፉን ምርትና ምርታማነት ለማስፋት መጣር ይገባል።

መንግሥት ከውጭ የሚገባውን ስንዴ በአገር ውስጥ ምርት ለመሸፈን በአፋር፣ በኦሮሚያና በደቡብ እና በሌሎችም አካባቢዎች በሚገኙ ሥፍራዎች ላይ የበጋ ስንዴ ልማት ሥራ እያከናወነ ይገኛል።

prosperity

Design a site like this with WordPress.com
Get started