“የጋራ ግብ” የመደመር አንዱ መሠረታዊ ጉዳይ ነው ስንል መደመር ልዩነትን ተሻግሮ ለጋራ ዓላማና ጥቅም መሰለፍን ስለሚመርጥ ነው።በእያንዳንዱ ልዩነት ውስጥ የጋራ ግብን መሠረት አድርጎ መተባበርና ውጤት ማምጣት ይቻላል ብሎ ታሳቢ ያደርጋል። የአድዋ ድል እውን የሆነው በውስጣችን የነበረውን ልዩነት የተሻገረ የጋራ ግብ ስለያዝን ለዚያ ስለተሰለፍን ነው።
የጋራ ግብ የጋራ ህልውናንና የጋራ ድልን ያቀዳጃል።ለጋራ ግብ መሰለፍ ጤናማ የሆነና ሚዛኑ የተጠበቀ ትብብርና ፉክክር እንዲኖርና ኃይላችን መሠብሰብ እንድንችል የሚያደርግ ነው።

መልካም ቀን ይሁንልዎ!
ኮልፌ ወረዳ 06 ብልፅግና ፓርቲ

ከአፍሪካ ኅብረት ስብሰባ ጎን ለጎን ከአሜሪካ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ረዳት ዳይሬክተ ሜሪ ካትሪን ፒ ጋር የሁለትዮሽ ውይይት አድርጌያለሁ። በሰላም ስምምነቱ አፈጻጸም ላይ ተወያይተናል።

I held a bilateral meeting with U.S Assistant Secretary of State, Mary Catherine Phee on the margins of the #AUSummit where we discussed progress made on implementation of the Peace Agreement.
ጠ/ሚ ዐብይ አህመድ

በአዲስ አበባ ከተማ በ3.8 ቢሊዮን ብር ወጪ ተገዝተው ወደ ስራ የሚገቡት ዘመናዊ የ100 የከተማ አውቶብሶች የአገልግሎት ማስጀመሪያ ስነስርዓት በመስቀል አደባባይ እየተከናወነ ይገኛል፡፡

ፕሬዝዳንት ኢማኑኤል ማክሮንን በማግኘቴ ደስ ብሎኛል። በፓሪስ ስለተደረገልን አቀባበል እናመሰግናለን። በሁለቱ ሀገራት መካከል ያለው ግንኙነት እየጠነከረ ሲሄድ፣ ወደ ላቀ ኢኮኖሚያዊ ውጤት እንደሚሸጋገር እምነቴ ነው። የፈረንሳይ ኩባንያዎች በኢትዮጵያ የሚያደርጉትን ኢንቨስትመንት ለማበረታታት እወዳለሁ።

Pirezdaanti Imaanu’el Makrooniin walarguukootti gammadeera. Simannaa Paarisitti nuuf taasifameef nan galateeffadha. Walittidhuheenyi biyyoota lachan gidduu jiru cimaa yoo deemu, gara bu’aa dinagdee olaanaatti akka cehun amana. Kaampaaniiwwan Faransaay invastimentii Itoophiyaatti godhan jajjabeessuun barbaada.

Always good to meet my friend President Emmanuel Macron. Thank you for the warm welcome to Paris. As the relations between our two countries’ progress, I’m very confident that it will translate into strengthened economic outcomes. We very much welcome investments by French companies in Ethiopia.

ጠቅላይ ሚኒሰትር ዐብይ አህመድ

የበለጸገች ኢትዮጵያን እውን ማድረግ !!

በፓርቲያችን ፕሮግራም ላይ በግልጽ እንደተመለከተው የብልጽግና ፓርቲ ጥቅል ዓላማ ፥’የበለጸገች ኢትዮጵያን እውን ማድረግ’ ነው፡፡

ብልጽግና ስንል ፈርጀ ብዙ ትርጓሜን ያዘለ ነው፡፡ የኢኮኖሚ፣ ፖለቲካ እና ማኅበራዊ ገጽታ አለው።

የኢኮኖሚ ብልጽግና የሕዝብ መሠረታዊ ፍላጎቶች በተገቢና በዘላቂነት ለማሟላት የሚያስችል ፈጣን እና ሁለንተናዊ ዕድገትን በማስመዝገብ፣ ዓለም አቀፋዊ ተወዳዳሪነት ያለው ኢኮኖሚ በመገንባት ፍትሐዊ ተጠቃሚነትን ማረጋገጥና የሕዝብን ድህነትና ኋላቀርነትን ለመቅረፍ መቻልን ያካተተ ነው።

የፖለቲካ ብልጽግና ስንል ለዴሞክራሲ ባህል ማበብ አስፈላጊ የሆኑ ተቋማትን በመገንባት፣ የሕዝቦች ነጻነትና እኩልነት ተረጋግጦ፣ ሁሉም ኢትዮጵያውያን ሰብአዊ እና ዴሞክራሲያዊ መብቶቻቸው ተከብረውላቸው የሚኖሩባት፣ ኅብረ ብሔራዊ አንድነቷ የተረጋገጠ፣ ፌዴራላዊት ዲሞክራሲያዊት ኢትዮጵያን ጽኑ መሠረት ላይ ማቆም ነው።

የኢኮኖሚ ብልጽግና ስንል ደግሞ የሕዝባችን ሰፊ ክፍል የሆነውን አርሶ አደር፣ ወጣት፣ ሴቶች እንዲሁም ዝቅተኛ ገቢ ያላቸውን ዜጎች ማዕከል ያደረገ አካታች የኢኮኖሚ ሥርዓት በመገንባት የሕዝባችንን የጋራ ኢኮኖሚያዊ ብልጽግናን የማረጋገጥ ዓላማ ይኖረዋል።

በተረጋጋ የማክሮ ኢኮኖሚ አስተዳደር ማዕቀፍ ውስጥ የግሉን ዘርፍና ሌሎች የኢኮኖሚ ተዋናዮችን ተሳትፎ በማጎልበት ምርታማነትን በላቀ ደረጃና ቀጣይነት ባለው መልኩ የሚያሳድግ እንዲሆን ያደርጋል።

በዚህም መሠረት ፓርቲያችን ጥራት ያለውና ዘላቂ የኢኮኖሚ ዕድገትና ልማት እንዲሁም ፍትሐዊ ተጠቃሚነትን የሚያረጋገጥ አረንጓዴ ኢኮኖሚ በመገንባት ሀገራችንን ወደ ብልጽግና ጎዳና ለማሸጋገር ያልማል።

ማኅበራዊ ብልጽግና ማለት ደግሞ መልካም ሀገራዊ ወጎችን፣ ዕሴቶችን እና ባህሎችን በማዳበር በሥነ-ምግባር የታነፀ ትውልድ ማፍራት፣ በአካልና በአእምሮው የዳበረ ጤናማ ዜጋ መፍጠር፣ ከአስከፊ ማኅበራዊ ችግር የተጠበቀ ኅብረተሰብ መገንባት እና በሕዝቦች መካከል አዎንታዊ ሰላም በመፍጠር ሁለንተናዊ ብልጽግናን ማረጋገጥ የፓርቲያችን ጥቅል ዓላማዎች ናቸው።

Prosperity

Design a site like this with WordPress.com
Get started